የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ባለፈው ስድስት ወር ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት 908 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን አስታወቀ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ባለፈው ስድስት ወር ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት 908 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን አስታወቀ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ሻፊ ኡመር እንዳስታወቁት ይህ ገቢ የተገኘው ወደ አለም ገበያ ከተላከ 204,000 ቶን የቡና ምርት ነው። ሻፊ አክለውም በቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ምርቶች ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች እና የተጠናከረ ስራ፤ የውጭ የቡና ንግድ እንዲጠናከር እና ገቢዉ እድገት እንዲኖረው አስተዋፅኦ አድርጓል።በተያዘው አመት መንግስት 400,000 ቶን ቡና ወደ ውጭ ለመላክ እና 2 ቢሊዩን ዶላር ለማስገባት እቅድ ይዟል። ባለስልጣኑ በተያዘው የምርት ዘመን ከነበረዉ የምርት እቅድ እና በባለፈው አመት ከነበረው ምርት የተሻለ የቡና ምርት ዘንድሮ ተገኝቷል ማለቱን ፋና ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ   @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0