በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ቀደምት ሰዎች የላቀ መሳሪያ የመሥራት አቅም እንደነበራቸው ጥናት አመለከተ

ሰብስክራይብ
በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ቀደምት ሰዎች የላቀ መሳሪያ የመሥራት አቅም እንደነበራቸው ጥናት አመለከተ በእስራኤላዊው ፓሊዮአንትሮፖሎጂስት ኤሬላ ሆቨርስ እና በእየሩሳሌም የዕብራይስጥ ዩኒቨርስቲ አርኪዮሎጂስት ተገኑ ጎሳ የተመራው አዲስ ዓለም አቀፍ ጥናት፤ የፕሌይስቶሲን ዘመን ቀደምት ሰዎች ለተለያዩ መሳሪያዎች የሚጠቀሟቸውን ድንጋዮች ሲመርጡ አሰላስለው እንደነበር አሳይቷል። በኢትዮጵያ መልካ ዋኬና የተደረገ ቁፋሮ የመሳሪያ ባለሙያዎች ቁሶችን የሚመርጡት የተለያዩ ድንጋዮች የተለየ ስራ እንዴት ማከናወን እንደሚችሉ በመገንዘብ እንጂ በዘፈቀደ እንዳልነበር ጠቁሟል። ፖርቹጋላዊው ተመራማሪ ጆአዎ ማሬይሮስ "ቁሳቁሶቹ ታስበው መመረጣቸው የመሳሪያዎቹ የገጽታ ለውጥ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፣ ይህም በአርኪኦሎጂ ግኝቶች ላይ ያለው ልዩነት በዘፈቀደ እንዳልሆነ ያሳያል" ብለዋል። ይህ የመጀመሪያ ጥናት ስለ አቹሊያን የአርኪኦሎጂ ኢንዱስትሪ የመሣሪያ አሠራር ግንዛቤ የሚሰጥ እንደሆነ ተገልጿል። ቀጣይ ጥናት የመሳሪያ አሰራር እንዴት የጥሬ ዕቃዎች ምርጫ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ እንደሚመረምር የሚጠበቅ ሲሆን፤ የቀደምት ሰዎች ውሳኔ በዝግመተ ለውጥ እና ከአካባቢያቸው ጋር የነበራቸው መስተጋብር ላይ የነበረውን ወሳኝ ሚና ያሳያል ተብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0