ከ200 በላይ የኬንያ ፖሊሶች የወሮበላ ቡድኖችን ለመዋጋት የሄይቲን ተልዕኮ ተቀላቀሉ የወሮበላ ቡድኖችን አመጽ ለመዋጋት እና ሀገሪቱን ለማረጋጋት በተቋቋመው የተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ አካል የሆኑ ተጨማሪ 217 የኬንያ ፖሊስ መኮንኖች፤ ቅዳሜ እለት ሄይቲ ገብተዋል ሲል የኬንያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል። መኮንኖቹ ሲቪሎችን እንደሚጠብቁ፣ የህዝቡን ሰላም እንደሚያስከብሩ እና የሄይቲን ሕግ የማስከበር አቅም እንደሚደግፉም ተገልጿል። ግዳጃቸው ቅኝት፣ የማህበረሰብ ፖሊስ አገልግሎት እና የአካባቢውን ሕግ አስከባሪዎች ማሰልጠን ያካትታል። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ኬንያ ባለፈው ሰኔ ወር 400 መኮንኖችን ባሰማራችበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ በፖሊስ አባላቶቹ የሙያ ሥነምግባር እና ብቃት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ከአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ጃማይካ እና ሴኔጋል ድጋፍ ላገኘው ተልዕኮ ከ420 ሚሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተሰብስቧል። ሄይቲ በወንበዴዎች ጥቃት፣ አፈና እና የፖለቲካ አለመረጋጋት መታመሷን ተከትሎ የሀገሪቱን ደህንነት ለመመለስ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ለመሻት ተገዳለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ከ200 በላይ የኬንያ ፖሊሶች የወሮበላ ቡድኖችን ለመዋጋት የሄይቲን ተልዕኮ ተቀላቀሉ
ከ200 በላይ የኬንያ ፖሊሶች የወሮበላ ቡድኖችን ለመዋጋት የሄይቲን ተልዕኮ ተቀላቀሉ
Sputnik አፍሪካ
ከ200 በላይ የኬንያ ፖሊሶች የወሮበላ ቡድኖችን ለመዋጋት የሄይቲን ተልዕኮ ተቀላቀሉ የወሮበላ ቡድኖችን አመጽ ለመዋጋት እና ሀገሪቱን ለማረጋጋት በተቋቋመው የተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ አካል የሆኑ ተጨማሪ 217 የኬንያ ፖሊስ መኮንኖች፤ ቅዳሜ... 19.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-19T18:52+0300
2025-01-19T18:52+0300
2025-01-19T19:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ከ200 በላይ የኬንያ ፖሊሶች የወሮበላ ቡድኖችን ለመዋጋት የሄይቲን ተልዕኮ ተቀላቀሉ
18:52 19.01.2025 (የተሻሻለ: 19:14 19.01.2025)
ሰብስክራይብ