በሱዳን የደረሰ የድሮን ጥቃት የኃይል መቋረጥ አስከተለ

ሰብስክራይብ
በሱዳን የደረሰ የድሮን ጥቃት የኃይል መቋረጥ አስከተለ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ፈጽሞታል የተባለው የድሮን ጥቃት፤ በሱዳን ጦር ቁጥጥር ስር ባሉ አብዛኛዎቹ ቦታዎች ላይ የኃይል መቋረጥ እንዳስከተለ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ጥቃቱ የሜሮዌ ግድብ፣ አል ሹክ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ጨምሮ ቁልፍ በሆኑ የኃይል ማመንጫዎች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ተገልጿል። በሜሮዌ ግድብ ላይ የተካሄደውን ጥቃት ተከትሎ፤ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የኃይል መቆራረጡ እንደጀመረ ነው የተሰማው። ተጨማሪ የቴክኒክ ችግሮች በናይል ወንዝ እና በቀይ ባህር ግዛቶች ላይ ተፅዕኖ አሳድረዋል። ቅዳሜ በአል-ሹክ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት በገዳረፍ፣ ካሳላ እና ሴናር ግዛቶች የኃይል መቋረጥ አስከትሏል። የኃይል መቆራረጥ የደረሰባቸው አካባቢዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን እንደሚያስጠልሉ ዘገባው ገልጿል። የመብራት መቆራረጡ የሆስፒታሎች፣ የትምህርት ቤቶች፣ የዳቦ ቤቶች እና የውሃ ተቋማትን እንቅስቃሴ አቃውሷል። የኦምዱርማን ነዋሪዎችም ከአባይ ወንዝ ውሃ ለመቅዳት ተገደዋል። መሐንዲሶች የሜሮው ኃይል ማመንጫን ጣቢያ ወደነበረበት ለመመለስ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፤ ጥረቱ እስካሁን ስኬታማ እንዳልሆነ ዘገባዎች አመልክተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0