ቲክ ቶክ አሜሪካ ውስጥ መስራት እንዳቆመና መተግበሪያው ከአፕ ስቶሮች እንደተነሳ ተሰማ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የቲክ ቶክ ተጠቃሚዎች የማህበራዊ ትስስር ገጹ ከጥር 11 በኋላ በሀገሪቱ መስራቱን እንደሚያቆም ማሳወቂያዎች ደርሷቸዋል። ተጠቃሚዎች ከቲክ ቶክ መተግበሪያ የደረሳቸውን ማሳወቂያ ስክሪን ሹት በመድረግ ኤክስ (X) ላይ አጋርተዋል። "በዩናይትድ ስቴትስ ቲክ ቶክን የሚከለክል ህግ ወጥቷል። በዚህም ለጊዜው ቲክ ቶክን መጠቀም አይችሉም ማለት ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ሥራ ሲገቡ ቲኪ ቶክን ለመመለስ ከእኛ ጋር እንደሚሰሩ በመግለጻቸው እድለኞች ነን። እባክዎትን ይጠብቁን!" ይላል ማስታወቂያው። የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጥር 11 ጀምሮ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ስራ ላይ የሚውለው እገዳ እንዲራዘም በቲክ ቶክ በኩል የቀረበውን ጥያቄ፤ አርብ እለት ውድቅ እንዳደረገ አርአይኤ ኖቮስቲ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተመልክቶ ዘግቧል። ኩባንያው እገዳው በአሜሪካ ሕገ-መንግሥት መሰረት የመናገር ነፃነትን የሚጻረር ነው ሲል ተከራክሯል። ዋይት ሀውስ የቻይናውን ማህበራዊ ትስስር ገጽ የዩናይትድ ስቴትስ እጣ ፈንታ በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ በትራምፕ አዲሱ አስተዳደር ሊወሰን ይገባል ብሏል። የቻይና መንግሥት የተጠቃሚዎችን መረጃ ሊጠይቅ ወይም ፕሮፓጋንዳ ለማሰራጨት ሊጠቀምበት ይችላል የሚል ፍራቻ ያላቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት፤ ቲክ ቶክ ላይ ከፍተኛ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል። የቲክቶክ ባለቤት የሆነው ኩባንያ እነዚህን ስጋቶች እንደማይቀበል በተደጋጋሚ ገልጿል። ቲክ ቶክ በአሜሪካ 170 ሚሊዮን የሚደርሱ ተጠቃሚዎች አሉት።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ቲክ ቶክ አሜሪካ ውስጥ መስራት እንዳቆመና መተግበሪያው ከአፕ ስቶሮች እንደተነሳ ተሰማ
ቲክ ቶክ አሜሪካ ውስጥ መስራት እንዳቆመና መተግበሪያው ከአፕ ስቶሮች እንደተነሳ ተሰማ
Sputnik አፍሪካ
ቲክ ቶክ አሜሪካ ውስጥ መስራት እንዳቆመና መተግበሪያው ከአፕ ስቶሮች እንደተነሳ ተሰማ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የቲክ ቶክ ተጠቃሚዎች የማህበራዊ ትስስር ገጹ ከጥር 11 በኋላ በሀገሪቱ መስራቱን እንደሚያቆም ማሳወቂያዎች ደርሷቸዋል። ተጠቃሚዎች ከቲክ... 19.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-19T13:08+0300
2025-01-19T13:08+0300
2025-01-19T13:54+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ቲክ ቶክ አሜሪካ ውስጥ መስራት እንዳቆመና መተግበሪያው ከአፕ ስቶሮች እንደተነሳ ተሰማ
13:08 19.01.2025 (የተሻሻለ: 13:54 19.01.2025)
ሰብስክራይብ