የቡርኪናፋሶ የፀጥታ ሚኒስትር ሀገሪቱን ከኮትዲቯር በሚያዋስነው ድንበር ጎብኝት አደረጉ

ሰብስክራይብ
የቡርኪናፋሶ የፀጥታ ሚኒስትር ሀገሪቱን ከኮትዲቯር በሚያዋስነው ድንበር ጎብኝት አደረጉ እንደ ሚኒስቴሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ማሃማዱ ሳና የዪንደሬ የፍቸሻ ጣቢያን አርብ እለት ጎብኝተዋል። ሚኒስትሩ የጸጥታ ሁኔታውን ለማረጋገጥ የተወሰዱ እርምጃዎችን ገምግመዋል። "የእናንተ ጥረት፣ ፅናት እና ቁርጠኝነት የሀገራችንን ደህንነት ለማስጠበቅ ወሳኝ ምሰሶዎች ናቸው። በቀጣይም ይዞታችንን በተጠንቀቅ መያዙን እንቀጥል" ሲሉ ለመከላከያና የፀጥታ አካላት እንዲሁም ለመከላከያ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተናግረዋል። የሳህል ሀገራት ህብረት አባል ዜጎችን የድንበር እንቅስቃሴ ምቹ ማድረግም ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው አክሎ ገልጿል። "ትብብር እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የተጓዦች መቀበያ እና ፈጣን አገልግሎት መስጫ ክፍሎች እንደተዘጋጁ" በመግለጫው ተመላክቷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0