ሱዳን ውስጥ ዜጎች ተገድለዋል መባሉን ተከትሎ በደቡብ ሱዳን በተነሳው ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት በመላ ሀገሪቱ የሰዓት እላፊ ታወጀ

ሰብስክራይብ
ሱዳን ውስጥ ዜጎች ተገድለዋል መባሉን ተከትሎ በደቡብ ሱዳን በተነሳው ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት በመላ ሀገሪቱ የሰዓት እላፊ ታወጀ ከምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት የሚቆየውን የሰዓት እላፊ አዋጅ በቴሌቭዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር ያስታወቁት የፖሊስ አዛዥ አብርሀም ፒተር ማንዩአት "ፖሊስ የትኛውንም አይነት ጥሰት አይታገስም" ብለዋል። ሁከቱ በዋነኛነት በዋና ከተማዋ ጁባ በሚገኙ የሱዳናውያን የንግድ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ቢያንስ የሶስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱን እና ሰባት መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ብጥብጡ በሱዳን ድንበር አቅራቢያ ወደምትገኘው አዊል ተዛምቶ ሶስት ቤቶች ተቃጥለዋል። የጸጥታ ኃይሎች የሱዳን ነዋሪዎችን ደኅንነታቸው ወደሚጠበቅበት ቦታ ለማዛወር እየሰሩ ነው። አመፁ የሱዳን ጦር እና ጥምር ቡድኖች በቅርቡ ዋድ ማዳኒ ከተማን ከአማፅያኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ባስለቀቁበት ወቅት፤ የደቡብ ሱዳን ዜጎችን ገድለዋል የሚል ክስ ከቀረበባቸው በኋላ የመጣ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የሱዳን ጦር ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ይደግፋሉ ተብለው በተጠረጠሩ ንፁሀን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትን ጨምሮ "የተነጠሉ ጥቃቶችን" አውግዟል። የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሱዳን አምባሳደርን ጠርተው ካነጋገሩ በኋላ "በቁጣ ምክንያት ልቦናችን ሊጋረድ ወይም በሀገራችን የሚገኙ የሱዳን ነጋዴዎችና ስደተኞችን በጠላትነት ልንመለከት አይገባም" ሲሉ አሳስበዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0