ኢትዮጵያ እና ኢራን ብሪክስን ተጠቅመው ግኑኝነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የኢራን አፈ-ጉባኤ ተናገሩ የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሐመድ ጋሊባፍ፤ አርብ እለት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በአዲስ አበባ ባደረጉት ውይይት፤ የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በኢኮኖሚ፣ ባህል እና ፖለቲካ ትስስር ሊሰፋ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል። ኢራን እና ኢትዮጵያ በእስያ እና አፍሪካ የሚገኙ፤ በአንዳንድ ኃያላን የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲዎች ሳቢያ የሚፈተኑ ወሳኝ ሀገራት መሆናቸውንም አንስተዋል። የሁለቱ ሀገራት ደማቅ ባህል እና ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ያላት ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ በኢኮኖሚ፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መስኮች ትብብርን ለማስፋት ልዩ እድል ይፈጥራል ሲሉ የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤው ተናግረዋል። "የብሪክስ ቡድንን አቅም የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማሳደግ እና ትብብራችንን ለማጠናከር ልንጠቀምበት ይገባል" ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ኢራን በፈረንጆቹ 2024 ጥር ወር ብሪክስን በይፋ ተቀላቅለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢራን ከሌላኛዋ የብሪክስ አባል ሀገር ሩሲያ ጋር ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነት አርብ እለት ተፈራርማለች። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ እና ኢራን ብሪክስን ተጠቅመው ግኑኝነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የኢራን አፈ-ጉባኤ ተናገሩ
ኢትዮጵያ እና ኢራን ብሪክስን ተጠቅመው ግኑኝነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የኢራን አፈ-ጉባኤ ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ እና ኢራን ብሪክስን ተጠቅመው ግኑኝነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የኢራን አፈ-ጉባኤ ተናገሩ የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሐመድ ጋሊባፍ፤ አርብ እለት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በአዲስ አበባ ባደረጉት ውይይት፤ የሁለቱ... 18.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-18T13:10+0300
2025-01-18T13:10+0300
2025-01-18T13:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኢትዮጵያ እና ኢራን ብሪክስን ተጠቅመው ግኑኝነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የኢራን አፈ-ጉባኤ ተናገሩ
13:10 18.01.2025 (የተሻሻለ: 13:44 18.01.2025)
ሰብስክራይብ