የኢትዮጵያ የድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከል ስራ ጀመረ 

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከል ስራ ጀመረ  ለሀገሪቱ ፖሊስ የመጀመሪያ የሆነው የድሮን ቴክኖሎጂ ማዕከል፤ የፖሊስ መኮንኖች በቴክኖሎጂ የታገዘ የፖሊስ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችላቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ተናግረዋል። ድሮኖቹ ከከተማ ፀጥታ ቁጥጥር ባሻገር የድንበር ፀጥታን ጨምሮ የኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡ ማዕከሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከአፍሪካ አምስቱ ምርጥ የፖሊስ ተቋማት ውስጥ ለመግባት እያደረገ ያለውን ጥረት ያግዛል መባሉንም የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0