ጥቂት የፍፃሜ ስራዎች ብቻ የቀሩት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት 97.6 በመቶ ተጠናቀቀ በአፍሪካ ግዙፉ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ ወደ 625 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ፤ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ይህ ከ14 ዓመት በፊት ከነበረው የግድቡ የመነሻ ግምት ወጪ ጋር የሚስተካከል ነው። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት ሁለት ተርባይኖችን በመጠቀም 1፣200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን፤ ሲጠናቀቅም 5፣150 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል። 42 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ አከማችቶ የሚገኘው ግድቡ፤ ሲጠናቀቅ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የማከማቸት አቅም ይኖረዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ሱዳን እና ግብፅ መካከል፤ በውሃ አቅርቦት እና ቁጥጥር ዙርያ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አለመግባባትን አስከትሏል። በመስከረም 2024 ግብፅ ጉዳዩን በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በይፋ በማንሳት፤ ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የምትከተለው አካሄድ አለማቀፋዊ ህግጋትንና በ2015 ሶስቱ ሀገራት የተፈራረሙትን ስምምነት የሚጥስ ነው ስትል ተከራክራለች። ኢትዮጵያ በምላሹ የግብፅን ጥያቄ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በፃፈችው ደብዳቤ ውድቅ አድርጋለች። ኢትዮጵያ የግድቡ አሞላል ሂደት የሶስትዮሽ የባለሙያዎች ቡድን ያወጣውን መመሪያ የተከተለ መሆኑንም ገልጻለች። ግብፅ ሌሎች ሀገራትን ሊጎዱ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ከማካሄድ እንድትቆጠብ በማስጠንቀቅ፤ ቅንጅታዊ የውሳኔ አሰጣጥ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥታለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ጥቂት የፍፃሜ ስራዎች ብቻ የቀሩት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት 97.
ጥቂት የፍፃሜ ስራዎች ብቻ የቀሩት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት 97.
Sputnik አፍሪካ
ጥቂት የፍፃሜ ስራዎች ብቻ የቀሩት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት 97.6 በመቶ ተጠናቀቀ በአፍሪካ ግዙፉ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ ወደ 625 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ፤ የህዳሴ ግድብ... 17.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-17T10:40+0300
2025-01-17T10:40+0300
2025-01-17T11:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий