የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የሩሲያ -ኢትዮጵያን በይነመንግስታት ኮሚሽንን በምክትል ሰብሳቢነት እንዲመሩ ተሾሙ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የሩሲያ -ኢትዮጵያን በይነመንግስታት ኮሚሽንን በምክትል ሰብሳቢነት እንዲመሩ ተሾሙ የሩሲያ መንግስት ማክሲም ሬሼትኒኮቭን  የኢትዩጵያ-ሩሲያ በይነመንግስታት (አይጅሲ) የኢኮኖሚ፣ ሳይንስ እና ቴክኒካዊ ትብብር መድረክ  ምክትል ሰብሳቢ ሆኖው መሾማቸውን አስታውቋል። "ኢትዩጵያ የሩሲያ አስፈላጊ አጋር እና በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ካሉት ግዙፍ ኢኮኖሚዎች አንዷ ናት። አሁን ላይ በሩሲያ በኩል የተሾሙት ምክትል ሰብሳቢ በሀገራቱ መሀከል ያለውን የሁለትዩሽ ግንኙነትን በማጠናከር ትክክለኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዩች ላይ አብሮ ለመስራት የሩሲያን ፍላጎት የሚያሳይ ነው" በማለት የሩሲያ ኢኮኖሚ ልማት ምክትል ሚኒስትር ቭላድሚር አይልቼቭ በይፋዊ መግለጫ አስታውቀዋል። በጎርጎሮሳዊያኑ 1965 የተቋቋመው አይሲጄ በጂኦሎጂ፣ ኢነርጂ፣ ኢንዱስትሪ፣ ግብርና፣ ትምህርት እና በሌሎች የሁለትዮሽ ስምምነቶች ዙርያ ምቹ ሁኔታን ሲፈጥር ቆይቷል። ኢንሼቲቩ በመሀከለኛ -ደረጃ የልማት ፕሮግራም ሲመራ የቆየ ሲሆን ነዳጅ እና ዘይት፣ የኤሌትሪክ ኃይል፣ የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር፣ የጤና እና የግብርና ልማት ዘርፎችን ያካትታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ   @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0