በኬንያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በትምህርት ቤት ፈተና እና በተቃውሞዎች ወቅት የኢንተርኔት መዘጋት 75 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ማስከተሉን ጥናት ገለጸ

ሰብስክራይብ
በኬንያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በትምህርት ቤት ፈተና እና በተቃውሞዎች ወቅት የኢንተርኔት መዘጋት 75 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ማስከተሉን ጥናት ገለጸበብዛት በፈተና እና በተቃውሞ ወቅት ሆን ተብሎ ኢንተርኔት መዝጋት በኬንያ ከጎርጎርሳውያኑ 2023 ከነበሩት 15.6 ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ጋር ሲነጻጸር በ2024 ከ52.5 ሚሊዮን ህዝብ መካከል 22.7 ሚሊዮን ኬንያውያን ላይ ተጸዕኖ ማድረሱን ቶፕቴንቪፒኤን የተባለ ተቋም ጥናት ገለጸ። በሚታይ ሁኔታ በጎርጎሮሳውያኑ በ2024 በኬንያ ሁለት ዋና የኢንተርኔት መዘጋት ወይም የማህበራዊ ሚዲያ እገዳ ክስተቶች ብቻ እንደነበሩ  ቶፕቴንቪፒኤን ያሰባሰበው መረጃ አመላክቷል።▪ ኬንያ ከጎርጎሮሳውያኑ ህዳር 8 እስከ 29 ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰባት ሲሆን፤ ይህም የሆነው የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመጨረሻ ፈተና ወቅት የቴሌግራም ማህበራዊ ሚዲያ በሀገሪቱ ለ504 ሰዓታት በመዘጋቱ ነው። በዚህም 22  ሚሊዮን 710 ሺህ ተጠቃሚዎች ላይ ተጽዕኖ ያደረሰ ሲሆን 70,937,811 ዶላር ኪሳራም አስከትሏል።▪ከዚያም ሰኔ 25 ቀን በመንግስት የቀረቡትን አዳዲስ የታክስ እርምጃዎች በመቃወም በሰፊው በተደረጉ ተቃውሞዎች ምክንያት በመላ አገሪቱ ለሰባት ሰዓታት ያህል ኢንተርኔት ተቋርጧል። የኢንተርኔት መዘጋቱ እኩል ቁጥር ያላቸውን የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ላይ ተጽዕኖ ያደረሰ ሲሆን በዚህም ምክንያት 4,081,739 ዶላር ኪሳራ ደርሷል። ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮች ለ32,938 ሰዓታት የበይነመረብ መቋረጥ ያስከተለው ጠቅላላ ኪሳራ 1. 56 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን 111. 2 ሚሊዮን ሰዎች ላይም ተጽዕኖ አድርሷል። ኬንያ ከሱዳን እና ከኢትዮጵያ ቀጥሎ በኪሳራ መጠን ከቀጠናው ሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጥናቱ አመልክቷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ   @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0