የኢትዮ-ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበት 55ተኛ አመት መከበር ጀመረይህ በአል የተከበረው አዲስ አበባ በሚገኘው የወዳጅነት አደባባይ ፓርክ ውስጥ ነው። በኩነቱ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ ቻይናውያን አዲስ አመታቸውን አክብረዋል።ኩነቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምስጋኑ አረጋ፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሰደር ቼን ሃ፣ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ እና የቀድሞ የህዝብ ተወካዩች ምክርቤት አፈጉባኤ ፤ የዲቦራህ ፋውንዴሽን መሰራችን እና ሊቀመንበር አባዱላ ገመዳ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመውበታል።ኩነቱን በንግግር የከፈቱት አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በንግግራቸው በሁሉም ዘርፍ በኢትዮጵያ እና ቻይና መሀከል "በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ያለውን የእስትራቴጂክ አጋርነት" የማይቀየር እና ጥብቅ መሆኑን ተናግረዋል።ሚኒስትሩ ጨምረውም ባለፉት አምስት አስርት አመታት ሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ በጥንካሬ ሲሰሩ ነበር ብለዋል።"ለጎርጎሮሳውያኑ 2025 አዲስ አመት ባስተላለፉት መልእክት የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ የቻይናን አዲስ የዘመናዊነት ጉዞ መጀመርን አብስረዋል" ያሉት አምባሳደሩ ጨምረውም " ይህንን 55ተኛ በአል FOCAC ጉባኤ ውጤቶች ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደ መነሻ ነጥብ ያገለግላል፤ በሁለቱ ሀገራት መሀከል የተፈረመውን ስምምነት ወደ ዘመናዊ ለማሳደግ ይረዳል" በማለት አምባሳደሩ ተናግረዋል።ሁለቱም ሀገራት የብሪክስ አጋርነት አባልነታቸው ግንኙነታቸውን ይበልጥ ያሳድገዋል። በኩነቱ ላይ ከሁለቱም ሀገራት በተወጣጡ የባህል ቡድኖች ባህላዊ ጭፈራዎች ቀርበዋል በማለት ፋና ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮ-ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበት 55ተኛ አመት መከበር ጀመረ
የኢትዮ-ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበት 55ተኛ አመት መከበር ጀመረ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮ-ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበት 55ተኛ አመት መከበር ጀመረይህ በአል የተከበረው አዲስ አበባ በሚገኘው የወዳጅነት አደባባይ ፓርክ ውስጥ ነው። በኩነቱ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ ቻይናውያን አዲስ አመታቸውን አክብረዋል።ኩነቱ ምክትል... 13.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-13T20:30+0300
2025-01-13T20:30+0300
2025-01-13T20:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий