ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲን በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት የስልክ ውይይት ሊያደርጉ እንደሚችሉ የአሜሪካ ድህንነት አማካሪ አስታወቁ

ሰብስክራይብ
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲን በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት የስልክ ውይይት ሊያደርጉ እንደሚችሉ የአሜሪካ ድህንነት አማካሪ አስታወቁ" እስካሁን ድረስ ትክክለኛውን ማዕቀፍ አላስቀመጥንም። በዚህ ጉዳይ ላይ እየሰራን ነው፤ ነገር ግን በሚቀጥሉት ቀናት እና ሳምንታት ቢያንስ አንድ ጥሪ እንጠብቃለን፣ ስለዚህ ይህ አንድ እርምጃ ነው እና ከዚያ እንወስዳለን" ሲሉ የትራምፕ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ማይክ ዋልትዝ በኤቢሲ ስርጭት ላይ ተናግረዋል።ሁለቱ መሪዎች ሊወያዩባቸው ከሚገባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ "በጦር ሜዳ ላይ ያሉ ነገሮችን ማረጋጋት" ነው ያሉት የፀጥታ አማካሪው፤ ትራምፕ በሩሲያ ቁጥጥር ስር ያሉ ግዛቶችን መልሶ የመያዝ ሀሳብ እውን ሊሆን እንደማይች እንደሚገነዘቡና ሌሎችም ይህንን መረዳት መጀመራቸውን ገልጸዋል።ዋልትዝ በተጨማሪም የተኩስ አቁም ስምምነት ማሳካት ለሩሲያም ሆነ ለዩክሬን "በጣም አዎንታዊ የሆነ የመጀመሪያ እርምጃ" እንደሚሆንና ይህም ግጭቱን በድርድር ወደመፍታት ሊያመራ እንደሚችል ተናግረዋል።"ይህ ጉዳይ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መጠናቀቅ እንዳለበት ሁሉም ሰው ያውቃል። እያንዳንዱን ሩሲያውያንን ከዩክሬን ምድር ከእያንዳንዱ ኢንች እናባርራለን ማለት እውን የሚሆን አይመስለኝም ። ከክሬሚያም ቢሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እንኳን ያንን እውነታ እውቅና ሰጥተዋል። እናም መላው ዓለም ይህንን እውነታ እንዲረዳ ትልቅ እርምጃ ነው ብዬ አስባለሁ" ብለዋል ዋልዝ።በጎርጎሮሳውያኑ ሰኔ 2024 ፑቲን የዩክሬን ወታደሮች ከሩሲያ አዳዲስ ክልሎች እንዲወጡ እና ኬቭ ኔቶን ለመቀላቀል የያዘችውን ዕቅድ እንድታቋርጥ እንድታረጋግጥ ጨምሮ በዩክሬን ሰላም እንዲሰፍን ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። በነሃሴ ወር የዩክሬን ወታደሮች በሩሲያ ኩርስክ ክልል ላይ ጥቃት ከፈፀሙ በኋላ ፑቲን ድርድሩ የማይሆን ነው ብለዋል። የሞስኮ የሰላም ሀሳብ አልተተወም፣ ነገር ግን ሩሲያ እስካሁን ከዩክሬን ጋር ግንኙነት ማድረግ አትፈልግም።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ   @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0