ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኡጋንዳ ጦር ኃይል አዛዥ በትዊተር ገፃቸው ባጋሩት ቀስቃሽ ጸሁፍ ምክንያት ከካምፓላ ጋር ያላትን ግንኙነት ልታቋርጥ እንደምትችል አስጠነቀቀች

ሰብስክራይብ
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኡጋንዳ ጦር ኃይል አዛዥ በትዊተር ገፃቸው ባጋሩት ቀስቃሽ ጸሁፍ ምክንያት ከካምፓላ ጋር ያላትን ግንኙነት ልታቋርጥ እንደምትችል አስጠነቀቀች የኡጋንዳ ጦር አዛዥ ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባጋሩት ፅሁፍ፤ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን በማጥላላት እና በማንኳስስ ሀገሪቱ ላይ ንቀት በማሳየታቸው እና የወረራ ዛቻ በመሰንዘራቸው፤ ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት ለማቋረጥ እና የጋራ ፕሮጀክቶችን ለማቆም እያጤነች እንደሆነ ኡጋንዳ አስታውቃለች። "የሁለቱን ሀገራት ትብብር እና ወዳጅነት ከግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህ መግለጫዎች አሳሳቢ ናቸው" ሲሉ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴሬዝ ካይክዋምባ ዋግነር ተናግረዋል። ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ይፋዊ ማብራርያ ከኡጋንዳ ባለስልጣናት እንደምትጠብቅ የገለፁት ሚኒስትሩ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ ኪንሻሳ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመገምገም እንደምትገደድ አስጠንቅቀዋል። ውዝግቡ በምስራቅ ኮንጎ ሹጃአ የተሰኘ የጋራ ወታደራዊ ኦፕሬሽን እየተካሄደ ባለበት እና ጄኔራል ሙሁዚ የኤክስ ገጻቸውን ባቋረጡበት ወቅት የመጣ ነው። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሏቸው ጄኔራል ሙሁዚ፤ ገጻቸውን በመለኮታዊ መመሪያ መሰረት እንዳቋረጡ ገልጸዋል። “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ መመሪያ እና ቡራኬ…ለመልቀቅ እና በጦር ሰራዊቱ የኡጋንዳ ህዝቦች መከላከያ ኃይል ላይ ትኩረት የሚደረግበት ሰዓቱ አሁን ነው” ሲሉ ጽፈዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0