የሱዳኑ መሪ አል-ቡርሃን በማሊ የመጀመሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አደረጉ

ሰብስክራይብ
የሱዳኑ መሪ አል-ቡርሃን በማሊ የመጀመሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አደረጉ የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ለ48 ሰዓታት የወዳጅነት እና የስራ ጉብኝት ቅዳሜ እለት ባማኮ ገብተዋል። ከማሊ ሕዝብ ሳልቬሽን ብሔራዊ ኮሚቴ መሪ አሲሚ ጎይታ ጋር ከተገናኙ በኋላ፤ የሁለቱ ሀገራት ልዑካን በኩሉባ ቤተ-መንግሥት ውይይት እንዳካሄዱ የማሊ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ውይይቱ በጸጥታ ቀውሶች እና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙርያ በርካታ የጋራ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል። የማሊ ሕዝብ ለሱዳን ላደረገው የማያቋርጥ ድጋፍ ምሥጋና ያቀረቡት አል-ቡርሃን፤ "በተፈተነ አካባቢ የምንኖር ሁለት ወንድማማች ሀገሮች ነን" ብለዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢኮኖሚ፣ ጸጥታና ባህል የተለያዩ የትብብር መስኮችን በመለየት ግቦቹን ለማሳካት የጋራ ኮሚሽኖችን ስለማቋቋም ተወያይተዋል። በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ጥቅሞቻቸውን በጋራ ለመከላከል ያላቸውን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል። "በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች እምቅ አቅም ያላቸውን የትብብር እድሎች ለመቃኘት ነው የመጣሁት። ለአፍሪካ እና ክፍለ አህጉራችን የጋራ ራዕይ አለን" ሲሉ የሱዳኑ መሪ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0