የደቡብ ኮሪያ ቦይንግ አውሮፕላን ጥቁር ሳጥኖች አደጋው ከመድረሱ አራት ደቂቃ በፊት ስራ እንዳቆሙ ሪፖርት አመለከተ

ሰብስክራይብ
የደቡብ ኮሪያ ቦይንግ አውሮፕላን ጥቁር ሳጥኖች አደጋው ከመድረሱ አራት ደቂቃ በፊት ስራ እንዳቆሙ ሪፖርት አመለከተ መርማሪ ቦርዱ የበረራ መቅጃዎቹ ሥራ ያቆሙበትን ምክንያት እንደሚያጣራ ገልጿል። የአቪዬሽን ባለሙያዎች ይህ ሊሆን የቻለው አውሮፕላኑ ከወፎች መንጋ ጋር መጋጨቱን ተከትሎ፤ የሁለቱም ሞተሮች ሀይል ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ሊሆን እንደሚችል መናገራቸውን ዮንሃፕ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከባንኮክ ወደ ደቡብ ኮሪያዋ ሙአን ከተማ 181 ሰዎችን አሳፍሮ ይበር የነበረው የጄጁ አየር መንገድ ቦይንግ 737-800 በረራ 7ሲ 2216፤ ለማረፍ ሲሞክር ተንሸራቶ ከአጥር ጋር መጋጨቱ የሚታወስ ነው። ከአደጋው ​​ሁለት ሰዎች የተረፉ ሲሆን 179 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0