ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የአንካራውን ስምምነትን በቁርጠኝነት ለመፈጸም ተስማሙ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ በትናንትናው እለት ኢትዮጵያ ገብተዋል። ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል በቅርቡ የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ የመጣ ነው። ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በራስ ገዟ ሶማሊላንድ ዙርያ የገቡበትን ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት በቱርክ ሸምጋይነት ባለፈው ወር በፈረሙት የአንካራ ስምምነት ፈትተዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ፤ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ውክልና ወደነበረበት ለመመለስና ለማጠናከር መስማማታቸውን በጋራ ያወጡት የአቋም መግለጫ አመልክቷል። ቀጣናዊ ግንኙነትን ለማሻሻል፣ የጋራ መግባባትን ለማሳደግ እና የጋራ ዕድገት እንዲመጣ የጋራ ጥረትን በማጠናከር በትብብር ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የአንካራውን ስምምነትን በቁርጠኝነት ለመፈጸም ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የአንካራውን ስምምነትን በቁርጠኝነት ለመፈጸም ተስማሙ
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የአንካራውን ስምምነትን በቁርጠኝነት ለመፈጸም ተስማሙ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ በትናንትናው እለት ኢትዮጵያ ገብተዋል። ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል በቅርቡ የተደረገውን ስምምነት... 12.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-12T13:12+0300
2025-01-12T13:12+0300
2025-01-12T13:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий