የሱዳን ጦር በፈጥኖ ደራሽ ኃይል ስር የነበረውን የአል-ጃዚራ ግዛት ዋና ከተማ እንደተቆጣጠረ የመንግሥት ቃል አቀባይ ገለጹ 🪖 በጥምር ቡድኖች የሚደገፈው የሱዳን ጦር፤ የአል-ጃዚራ ግዛት ዋና ከተማ ዋድ ማዳኒን ከፈጥኖ ደራሽ ኃይል ፓራሚሊታሪ ቡድን መልሶ መያዙን፤ የመንግሥት ቃል አቀባይ እና የባህልና ማስታወቂያ ሚኒስትር ካሊድ አል-አይሰር አስታውቀዋል። “የእኛ ኃይሎች በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ቀሪ አማፂያንን በማጥራት ላይ ይገኛል" ሲሉ የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ተናግረዋል። ጦሩ ከአንድ ዓመት በላይ በአማጺያኑ ቁጥጥር ስር በነበረችው ከተማ በገሰገሰበት ወቅት፤ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱን ቀደም ሲል ገልጿል። ▪የሰራዊቱ አላማ ሁሉም የአል-ጃዚራ ግዛት እና ሱዳን ነጻ እስክትወጣ ድረስ መግፋቱን መቀጠል እንደሆነ አል-ጃዚራን በሚያዋስነው ሴናር ግዛት የሱዳን ጦር የልዩ ዘመቻ አዛዥ የሆኑት ፋት አል-አሊም አል-ሹብሊ ለአልጀዚራ ጋዜጠኛ ተናግረዋል። የዋድ ማዳኒ ነዋሪዎች የከተማዋን ነጻ መውጣት ተከትሎ ደስታቸውን ሲገልፁ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተሰራጭተዋልበእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሱዳን ጦር በፈጥኖ ደራሽ ኃይል ስር የነበረውን የአል-ጃዚራ ግዛት ዋና ከተማ እንደተቆጣጠረ የመንግሥት ቃል አቀባይ ገለጹ
የሱዳን ጦር በፈጥኖ ደራሽ ኃይል ስር የነበረውን የአል-ጃዚራ ግዛት ዋና ከተማ እንደተቆጣጠረ የመንግሥት ቃል አቀባይ ገለጹ
Sputnik አፍሪካ
የሱዳን ጦር በፈጥኖ ደራሽ ኃይል ስር የነበረውን የአል-ጃዚራ ግዛት ዋና ከተማ እንደተቆጣጠረ የመንግሥት ቃል አቀባይ ገለጹ 🪖 በጥምር ቡድኖች የሚደገፈው የሱዳን ጦር፤ የአል-ጃዚራ ግዛት ዋና ከተማ ዋድ ማዳኒን ከፈጥኖ ደራሽ ኃይል ፓራሚሊታሪ ቡድን... 12.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-12T12:32+0300
2025-01-12T12:32+0300
2025-01-12T13:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የሱዳን ጦር በፈጥኖ ደራሽ ኃይል ስር የነበረውን የአል-ጃዚራ ግዛት ዋና ከተማ እንደተቆጣጠረ የመንግሥት ቃል አቀባይ ገለጹ
12:32 12.01.2025 (የተሻሻለ: 13:14 12.01.2025)
ሰብስክራይብ