ብራዚል በብሪክስ የፕሬዝዳንትነት ጊዜዋ ትብብር እንጂ ግጭት እንደማትሻ የሀገሪቱ ዲፕሎማት ተናገሩ ብራዚል ተለዋጩን የብሪክስ ፕሬዝዳንትነትን ስትረከብ፤ ዓለም አቀፋዊ ውጥረቶችን እንደምታስቀር እና ዶላርን የመተካትም ሆነ ፀረ-ምዕራባውያን አቋም የመያዝ ፍላጎት የላትም ሲሉ፤ የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስያ እና የፓሲፊክ ውቅያኖስ ሴክሬታሪ እና የሀገሪቱ የብሪክስ ተወካይ ኤድዋርዶ ፓዔስ ሳቦያ ለፈረንሣይ ሚዲያ ተናግረዋል። "በብሪክስ አባላት መካከል የንግድ ልውውጥን ለመጨመር፣ ኢንቨስትመንቶችን ለመጨመር እና የግብይት ወጪዎችን ለመቀነስ እንፈልጋለን። ግብይቶቻችንን በየሀገራቱ ገንዘብ መፈፀምን በተመለከተ ውይይቶች አሉ፤ ነገር ግን ይህ በአስገዳጅ መንገድ አይደለም" ብለዋል ሳቦያ። ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ከብሪክስ ሀገራት አዲስ የብሪክስ መገበያያ እንደማይፈጥሩ ወይም የአሜሪካን ዶላር የሚተካ ሌላ መገበያያ እንደማይደግፉ መተማማኛ የማያገኙ ከሆነ፤ 100% ታሪፍ እንደሚጠብቃቸው በፈረንጆቹ ታህሳስ 2024 መጀመሪያ ተናግረዋል። "የብሪክስ አባላት ፀረ-ምዕራባውያን አይደሉም። በተቃራኒው ከ2008ቱ ቀውስ በኋላ ትላልቅ ኢኮኖሚዎች የዓለም ኢኮኖሚን በድጋሚ ለማስጀመር በሚደረገው ጥረት የብሪክስ ሀገራትን ትብብር ፈልገዋል። ብሪክስ የመገንባት ፍላጎትን ያመለክታል። የብሪክስ ሀገራት የመገንባት እንጂ ነገሮችን የማባባስ ፍላጎት የላቸውም" ብለዋል። የብሪክስ ትኩረት በተለያዩ ዘርፎች ትብብር መፍጠር እንዲሁም በዓለም አቀፍ መድረኮች በንቃት በመሳተፍ የደቡባዊው ዓለም ጥቅምን ማስጠበቅ እንደሆነ ዲፕሎማቱ አጽንኦት ሰጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ብራዚል በብሪክስ የፕሬዝዳንትነት ጊዜዋ ትብብር እንጂ ግጭት እንደማትሻ የሀገሪቱ ዲፕሎማት ተናገሩ
ብራዚል በብሪክስ የፕሬዝዳንትነት ጊዜዋ ትብብር እንጂ ግጭት እንደማትሻ የሀገሪቱ ዲፕሎማት ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
ብራዚል በብሪክስ የፕሬዝዳንትነት ጊዜዋ ትብብር እንጂ ግጭት እንደማትሻ የሀገሪቱ ዲፕሎማት ተናገሩ ብራዚል ተለዋጩን የብሪክስ ፕሬዝዳንትነትን ስትረከብ፤ ዓለም አቀፋዊ ውጥረቶችን እንደምታስቀር እና ዶላርን የመተካትም ሆነ ፀረ-ምዕራባውያን አቋም የመያዝ... 11.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-11T19:04+0300
2025-01-11T19:04+0300
2025-01-11T19:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ብራዚል በብሪክስ የፕሬዝዳንትነት ጊዜዋ ትብብር እንጂ ግጭት እንደማትሻ የሀገሪቱ ዲፕሎማት ተናገሩ
19:04 11.01.2025 (የተሻሻለ: 19:44 11.01.2025)
ሰብስክራይብ