🪖 የናይጄሪያ ወታደሮች በ2025 የመጀመሪያ ሳምንት 109 አሸባሪዎችን እንደገደሉ ተገለጸ

ሰብስክራይብ
🪖 የናይጄሪያ ወታደሮች በ2025 የመጀመሪያ ሳምንት 109 አሸባሪዎችን እንደገደሉ ተገለጸ የናይጄሪያ መከላከያ ሚዲያ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ኤድዋርድ ቡባ በዋና ከተማይቱ አቡጃ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ግምገማው በሚመለከተው ሳምንት ወታደሮቹ 109 አሸባሪዎችን ገድለው፣ 81 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ያዋሉ ሲሆን እና 43 ታጋቾችን አስለቅቀዋል" ብለዋል። እንደ ባለሥልጣኑ ገለጻ፤ የናይጄሪያ ወታደሮች ባካሄዱት ስኬታማ የውስጥ የደህንነት ኦፕሬሽን፤ የተጠረጠሩ የነዳጅ ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ ከፍተኛ መጠን ያለውና 618,756,470 ናይራ (397,115 ዶላር ገደማ) የሚገመት የተሰረቀ ድፍድፍ ዘይት የተመለሰ ሲሆን በኒጀር ዴልታ ሕገ-ወጥ የነዳጅ ማጣሪያ ቦታዎች ፈርሰዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች፣ ጥይቶች እና መሳሪያዎችም ተገኝተዋል። የናይጄሪያ ጦር በ2024 10,937 አሸባሪዎችን እንደገደሉ ቡባ ባለፈው ሳምንት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0