የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሕገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች እርቃናቸውን የታሰሩ 26 ኢትዮጵያውያን ማዳኑን አስታወቀ እንደ ፖሊስ ገለጻ በሰሜናዊ ጆሃንስበርግ ሳንድሪንግሃም ሰፈር በሚገኘው መኖሪያ ቤት፤ 15 የኢትዮጵያ ዜጎች ናቸው ተብለው የተገመቱ ግለሰቦች እርቃናቸውን ታስረው ተገኝተዋል። ለማምለጥ የሞከሩ ሌሎች 11 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ሌሎች ሶስት ኢትዮጵያውያን በሕገ-ወጥ የሰው ዝውውር እና ያለፈቃድ ሽጉጥ በመያዝ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል። ፖሊስ በቤቱ ላይ ኦፕሬሽን ከማካሄዱ በፊት ያለ ልብስ እና ሰነድ ከተያዙበት ክፍል፤ 30 የሚሆኑ ወንዶች በመስኮት አምልጠዋል ብሎ እንደሚያምን ፖሊስ አስታውቋል። ያመለጡት ግለሰቦች በአካባቢው ተደብቀው ሊሆን እንደሚችልም ፖሊስ ጠቁሟል። አብዛኞቹ ታሳሪዎች እንግሊዘኛ እንደማይናገሩ የገለጹት ኮሎኔል ፊላኒ ንኳላሴ፤ ከሱጡት ቃል መረዳት የተቻለው አልባሳት የሚሰጣቸው ከቤት ሲወጡ ብቻ ነው ብለዋል። ይህ መረጃ ፖሊስ ወደ 60 የሚጠጉ ሰዎች በቤቱ ውስጥ ተይዘው ነብር ብሎ ያስቀመጠው ግምት "ከእውነት የራቀ አይደለም" ተብሎ እንዲቆጥር አድርጎታል። የታሳሪዎቹ ማንነት እና እድሜ ዝርዝር እንዲሁም የታሰሩበት ጊዜ እና አላማ አልታወቀም።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሕገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች እርቃናቸውን የታሰሩ 26 ኢትዮጵያውያን ማዳኑን አስታወቀ
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሕገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች እርቃናቸውን የታሰሩ 26 ኢትዮጵያውያን ማዳኑን አስታወቀ
Sputnik አፍሪካ
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሕገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች እርቃናቸውን የታሰሩ 26 ኢትዮጵያውያን ማዳኑን አስታወቀ እንደ ፖሊስ ገለጻ በሰሜናዊ ጆሃንስበርግ ሳንድሪንግሃም ሰፈር በሚገኘው መኖሪያ ቤት፤ 15 የኢትዮጵያ ዜጎች... 10.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-10T17:42+0300
2025-01-10T17:42+0300
2025-01-10T18:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሕገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች እርቃናቸውን የታሰሩ 26 ኢትዮጵያውያን ማዳኑን አስታወቀ
17:42 10.01.2025 (የተሻሻለ: 18:14 10.01.2025)
ሰብስክራይብ