አዲስ አበባ በ6 ወራት ውስጥ 5 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን መሳብ እንደቻለች ተገለጸ

ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ በ6 ወራት ውስጥ 5 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን መሳብ እንደቻለች ተገለጸ በስድስት ወራት ውስጥ መዲናዋን ከጎበኙት ቱሪስቶች ውስጥ 4.6 ሚሊዮን የሚሆኑት የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ሲሆኑ፤ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑት የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች ናቸው። ከዚህ ከፍተኛ የጎብኚዎች ቁጥር የከተማ አስተዳደሩ 96 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንደቻለ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የቱሪስት መዳረሻዎች መስፋፋትና የኮሪደር ልማት ስራዎች፤ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት እንደሆነ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0