የጋቦን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በመጪው መጋቢት 13 እንደሚካሄድ የሀገሪቱ ርዕሰ መስተዳድር ይፋ አደረጉ

ሰብስክራይብ
የጋቦን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በመጪው መጋቢት 13 እንደሚካሄድ የሀገሪቱ ርዕሰ መስተዳድር ይፋ አደረጉ በጋቦን በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን የተቆጣጠረው ወታደራዊ አገዛዝ፤ የሽግግሩ ጊዜ የሚያበቃበት እና ሀገሪቱን ወደ ሲቪል ስርዓት ለመመለስ ቁልፍ እርምጃ ተደርጎ የተወሰደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በነሐሴ 2025 ለማካሄድ አቅዶ ነበር። በጋቦን በፈረንጆቹ ነሐሴ 30 ቀን 2023 ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ባካሄዱት መፈንቅለ መንግሥት፤ የአሊ ቦንጎ ኦንዲምባን የነሐሴ 26 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድል በመሰረዝ ስልጣን ተቆጣጥረዋል። በመቀጠልም ብራይስ ኦሊጊዊ ንጉዌማ የሽግግር ጊዜው ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል። በህዳር ወር በፀደቀው አዲሱ ሕገ-መንግሥት መሠረት ንጉዌማ በምርጫው ላይ መወዳደር ይችላሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0