ኢትዮጵያ እና ብራዚል በግብርና እና በምግብ ዋስትና መስኮች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ብራዚል በግብርና እና በምግብ ዋስትና መስኮች በጋራ ለመስራት ተስማሙ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ፤ ከብራዚል የማህበራዊ እድገት፣ የቤተሰብ ድጋፍ እና የድህነት ቅነሳ ሚኒስትር ዌሊንግተን ዲያስ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ ኢትዮጵያ እና ብራዚል በግብርና እና የምግብ ዋስትና መስኮች ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው። አምባሳደር ልዑልሰገድ፤ ኢትዮጵያ ግብርናን ለማዘመን፣ የምግብ ሉዓላዊነት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸውን ስራዎች እና የተመዘገቡ ውጤቶችን አስመልክቶ ለሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሚኒስትር ዌሊንግተን ዲያስ በበኩላቸው፤ ብራዚል ድህነትን በመቀነስ እና ረሃብን በመዋጋት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቧን ገልጸው፤ በድህነት ቅነሳ እና ረሃብን በመዋጋት ዙርያ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እና በቅርበት እንሰራለን ብለዋል። ሁለቱ ወገኖች በግብርና እና በምግብ ዋስትና መስክ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ረገድ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0