ታዋቂዋ የደቡብ አፍሪካ ዘፋኝና ተዋናይት ዊኒ ኩማሎ በድንገተኛ ህመም በ51 ዓመቷ አረፈችዜናው በቤተሰቧ የተረጋገጠ ሲሆን በትላንትናው እለት ወደ ሆስፒታል እየተጓዘች ማረፏን ተናግረዋል። የሞቷ ምክንያት እስካሁን አልተገለጸም። "እህቴ ታማ ነበር። ለትንሽ ቀናት ህመም አጋጥሟት ከበሽታዋ እየተፈወሰች እንደሆነ አስበን ነበር። ይሁን እንጂ ዛሬ ጠዋት ከበሽታዋ ሙሉ በሙሉ እንዳልዳነች ተረዳሁ። ወድያው ወደ ሆስፒታል አምርታ ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ እንደሞተች ተነገረ" በማለት እህቷ ሼፒ አኪፒል ለመገናኛ ብዙሃን ተናግራለች።ኩማሎ ከጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 1980 ዎቹ ጀምሮ ለበርካታ አሥርተ ዓመታት የዘለቀ ረጅም እና ስኬታማ የሥራ ቆይታ ነበራት። በዋናነት የምትታወቀው "ሊቭ ማይ ላይፍ" (Live My Life) በተሰኘው ዘፈኗ እና በህይወት ከሌለችው ብሬንዳ ፋሲን ጨምሮ ታዋቂ ከሆኑት የደቡብ አፍሪካ አርቲስቶች ጋር በጋራ ሆና በሰራችው ስራዎቿ ነው። ከሙዚቃዋ ባሻገር ኩማሎ በደቡብ አፍሪካ ታዋቂ በሆኑ የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎች ላይ ሰርታለች።በኃይለኛ ድምጿ እና ሁለገብነቷ የምትታወቀው ኩማሎ በሙዚቃም ሆነ በቴሌቪዥን ዘርፍ ትልቅ አሻራን ትታ አልፋለች። ከሴት ልጇ ሬታቢል ኩማሎ (እሷም ዘፋኝ ናት) እና ወንድ ልጇ ታቦ ኩማሎ ጋር አብራ ትኖር ነበር። “ለሙያዋ ያላት ዝንባሌ፣ ተሰጦ እና ቁርጠኝነቷ በኢንዱስትሪው እና በአድናቂዎቿ ልብ ላይ የማይጠፋ ነጥብ አስቀምጧል” ሲል አሳታሚዋ ካላዋ ጃዝሜ ሪኮርድስ ባወጣው መግለጫ ገልጿል። “እውነተኛ ተደናቂ” ሲል የጠራት ኩባንያው ሃይለኛ ድምጿ እና የማይረሳ አቀራረቧ ብዙዎችን አንቃቅቷል ብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ታዋቂዋ የደቡብ አፍሪካ ዘፋኝና ተዋናይት ዊኒ ኩማሎ በድንገተኛ ህመም በ51 ዓመቷ አረፈች
ታዋቂዋ የደቡብ አፍሪካ ዘፋኝና ተዋናይት ዊኒ ኩማሎ በድንገተኛ ህመም በ51 ዓመቷ አረፈች
Sputnik አፍሪካ
ታዋቂዋ የደቡብ አፍሪካ ዘፋኝና ተዋናይት ዊኒ ኩማሎ በድንገተኛ ህመም በ51 ዓመቷ አረፈችዜናው በቤተሰቧ የተረጋገጠ ሲሆን በትላንትናው እለት ወደ ሆስፒታል እየተጓዘች ማረፏን ተናግረዋል። የሞቷ ምክንያት እስካሁን አልተገለጸም። "እህቴ ታማ ነበር።... 08.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-08T20:28+0300
2025-01-08T20:28+0300
2025-01-09T10:54+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ታዋቂዋ የደቡብ አፍሪካ ዘፋኝና ተዋናይት ዊኒ ኩማሎ በድንገተኛ ህመም በ51 ዓመቷ አረፈች
20:28 08.01.2025 (የተሻሻለ: 10:54 09.01.2025)
ሰብስክራይብ