ሞስኮ በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የሁለት ሀገራት መፍትሄን በመደገፍ ቁልፍ ሚና እንደምትጫወት በተመድ የፍልስጤም መልዕክተኛ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ሞስኮ በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የሁለት ሀገራት መፍትሄን በመደገፍ ቁልፍ ሚና እንደምትጫወት በተመድ የፍልስጤም መልዕክተኛ ተናገሩ "ሩሲያ ይህን ጦርነት ለማስቆም እና ኡንርዋን (የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ) ለመጠበቅ እና ይህንን ወረራ የሚያስቆም እና የሁለቱ ሀገራት መፍትሄ መሬት ላይ ወርዶ እንዲታይ ለሚያስችል የፖለቲካ አድማስ ለመዘጋጀት ቁልፍ ሚና ትጫወታለች። ሩሲያ በነዚህ ሁሉ ሂደቶች ውስጥ ከኛ ጋር ናት" ሲሉ በተመድ የፍልስጤም አምባሳደር ሪያድ ማንሱር ለአርአይኤ ኖቮስቲ ተናግረዋል።ሩሲያ እና ፍልስጤም ጥብቅ የሆነ ወዳጅነት እና ትብብር አላቸው ያሉት አምባሳደሩ፤ ሞስኩ ጉዳዩን በተመለከት በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ እና በጸጥታው ምክር ቤት በምትይዘው አቋም ፍልስጤም በጣም ደስተኛ ነች" ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0