🪖 ሞዛምቢክ ወታደራዊ አገልግሎትን ፤ ፕሮፌሽናላዝምን እና ማቆየትን ለማሳደግ በሚል ወደ ስድስት ዓመት ማራዘሟን የመከላከያ ሚኒስቴር ባለስልጣን ተናገሩ

ሰብስክራይብ
🪖 ሞዛምቢክ ወታደራዊ አገልግሎትን ፤ ፕሮፌሽናላዝምን እና ማቆየትን ለማሳደግ በሚል ወደ ስድስት ዓመት ማራዘሟን የመከላከያ ሚኒስቴር ባለስልጣን ተናገሩበሞዛምቢክ ከጎርጎርሳውያኑ ጥር 2 እስከ የካቲት 28 የሚካሄደው ወታደራዊ ምዝገባ ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠሩ ዜጎች በሁለት ዓመት ምትክ  አምስት ወይም ስድስት ዓመት እንደሚያገለግሉ በመከላከያ ሚኒስቴር የሰው ሀብት ዳይሬክተር ጆርጅ ሊዮኔል በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።"ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እና አዲሱ ሕግ ከጸደቀ በኋላ በወታደራዊ አገልግሎት የሚካፈሉ ሰዎች በቀድሞው ሕግ ውስጥ እንደተጠቀሰው ለሁለት ዓመት ጊዜ ብቻ አያገለግሉም። ይልቁንም አዲሱ ህግ የአገልግሎት ጊዜውን በአጠቃላይ ወይም በልዩ ልዩ ኃይሎች ላይ በመመርኮዝ ወደ አምስት ወይም ስድስት ዓመታት አራዝሟል" ብለዋል።ይህ እርምጃ የታጠቁ ሀይሎችን ፕሮፌሽናል ለማድረግ የታቀደ ሲሆን፣ ይህም ለተመልማዮች ጠቃሚ ክህሎቶችንና ከአገልግሎታቸው በኋላ ለሲቪል ሕይወት ጠቃሚ ሙያዎችን በማቅረብ ፣ በዚህም የቆይታ መጠኖችን በማሻሻል እና በተደጋጋሚ ከስልጠና ምልመላ ጋር ተያይዞ የሚወጣ የመንግስት ወጪዎችን ለመቀነስ የሚረዳ ነው ሲሉ ሊዮኔል ተናግረዋል።የተራዘመው የጊዜ ገደብ የበለጠ አጠቃላይ ስልጠና እንዲሰጥ የሚያስችል መሆኑንና በወታደራዊው ሂደት ውስጥ ቀድሞውኑ አገልግሎቱን ለቀው ለመውጣት ጥያቄ እንዲቀርቡ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በእጅጉ የሚያሻሽል መሆኑ አክለው ገልጸዋል።"ከ18 እስከ 35 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ሴትና ወንድ የሞዛምቢክ ዜጎች እየተሳተፉ ሲሆን ዓላማውም 221,141 ወጣቶችን መመዝገብ ነው፤ ከእነዚህ ውስጥ 147,114 ወንዶች እና 74,027 ሴቶች ናቸው" ብሏል የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ። የሞዛምቢክ ፓርላማ በጎርጎሮሳውያኑ ታህሳስ 2023 የሀገሪቱን ወታደራዊ አገልግሎት ህግ ማሻሻያ ያፀደቀ ሲሆን ይህም የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት ከሁለት ወደ ስድስት ዓመት እንዲራዘም አድርጓል። ይህም ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ተግባራዊ ሆኗል። አዲሱ ውሳኔው ሐሙስ ዕለት በሀገሪቱ የተጀመረው የአሁኑ ወታደራዊ አገልግሎት ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0