ክሬምሊን ፑቲን እና ትራምፕ ወይም ሾልዝ ለመገናኘት ምንም አይነት አሁናዊ እቅድ እንደሌለ አረጋገጠ

ሰብስክራይብ
ክሬምሊን ፑቲን እና ትራምፕ ወይም ሾልዝ ለመገናኘት ምንም አይነት አሁናዊ እቅድ እንደሌለ አረጋገጠቅዳሜ ዕለት የጀርመን የሕግ አውጭ ሮድሪች ኪዝዌተር በኤክስ ትስስር ገጹ ላይ እንዳለው፤ የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ወደ ሞስኮ ተጉዘው ከጎርጎሮሳውያኑ የካቲት 23 በፊት ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ሊገናኙ እንደሚችሉ፤  እንዲሁም የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር ለሚገናኙበት ስብሰባ ደግሞ በመጋቢት ወር ቀጠሮ መያዙን “አመላካች ምልክቶች እየጨመሩ ነው" ብለዋል። ነገር ግን የትኛውን የመረጃ ምንጭ አልጠቀሰም።የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ግን በቭላድሚር ፑቲን እና ሾልዝ እንዲሁም በተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መካከል ስብሰባዎች እየተዘጋጁ ነው የሚለውን መረጃ  ውድቅ አድርገዋል።በተጨማሪም እሁድ ዕለት ሾልዝ ተቃዋሚው የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ህብረት አባል የሆኑት ኪሴዌተር ወደ ሞስኮ ሊጓዙ ነው  ማለታቸው ውድቅ በማድረግ "በጥልቀት ያልተረጋገጥ" በማለት ገልፀዋል። "ይህ የተሳሳተ መግለጫ ነው" ሲሉ ሾልዝ በፓርቲያቸው ስብሰባ ላይ መናገራቸውን አርኤንዲ ሚዲያ ቡድን ዘግቧል።ባለፈው ወር የጀርመኑ ጋዜጣ ስፒገል፤ በሲዲዩ ሾልዝ በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ሞስኮ "በሰላማዊ ተልዕኮ" ሊሄዱ ይችላል የሚል ጭምጭምታዎች መኖራቸው ዝግቧል። የጀርመን መንግስት የፕሬስ አገልግሎት ለአርአይኤ ኖቮስቲ እንደገለፀው ሾልዝ በቅርቡ ወደ ሞስኮ ጉብኝት ሊያደርጉ እንደሚችሉ የሚገልጹ የሚዲያ ዘገባዎች ልብ ወለድ ናቸው ብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0