የሩሲያ መርማሪዎች በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ በሩሲያ ጋዜጠኞች ላይ በተፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የወንጀል ክስ ከፈቱ" የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ ዋና የምርመራ ክፍል በሩሲያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 105 እና 167 (ግድያ እና ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሰዎችን የመግደል ሙከራ፤ ሆን ተብሎ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ) የተደነገጉ ወንጀሎችን መሠረት በማድረግ የወንጀል ክስ ከፍቷል" ሲል የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ በዛሬው እለት ለስፑትኒክ ተናግሯል። ቅዳሜ ምሽት የኤፍፒቪ ሰዉ አልባ አውሮፕላን በዶንዬትስክ-ጎርሎቭካ (ሆርሊቭካ) አውራ ጎዳና ላይ ከሚገኘው የግንኙነት መስመር ርቆ በሚገኝ የሲቪል ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት አድርሷል። የኢዜስቲያ ጋዜጣ ዘጋቢ አሌክሳንደር ማርቴሜያኖቭ የተገደለ ሲሆን የአርአይኤ ኖቮስቲ ዘጋቢ ማክሲም ሮማኔንኮ ጭንቅላቱን ተጎድቶ ራሱን በመሳቱ ሆስፒታል ገብቷል። የስራ ባልደረባው ሚካሄል ኬቭኪየቭ ደግሞ ሆስፒታል መግባት የማያስፈልገው ቀላል የጭንቅላት ጉዳት ደርሶበታል።በዶንዬትስክ የሚገኘው የብሎክኖት ጋዜጣ ሰራተኞች የሆኑት ስቬትላና ላሪና እና ኢዛቤላ ሊቤርማን በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፤ ህክምናቸውንም ወደ ሆስፒታሉ በመመላለስ ይቀጥላሉ።ኮሚቴው አክሎም በወንጀሉ ውስጥ የተሳተፉትን የዩክሬን ኃይል አደረጃጀቶች የሆኑ ግለሰቦችን ለመለየት እና በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ሁሉንም እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን ገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሩሲያ መርማሪዎች በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ በሩሲያ ጋዜጠኞች ላይ በተፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የወንጀል ክስ ከፈቱ
የሩሲያ መርማሪዎች በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ በሩሲያ ጋዜጠኞች ላይ በተፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የወንጀል ክስ ከፈቱ
Sputnik አፍሪካ
የሩሲያ መርማሪዎች በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ በሩሲያ ጋዜጠኞች ላይ በተፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የወንጀል ክስ ከፈቱ" የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ ዋና የምርመራ ክፍል በሩሲያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 105 እና 167 (ግድያ እና ሁለት ወይም... 05.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-05T19:25+0300
2025-01-05T19:25+0300
2025-01-05T19:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የሩሲያ መርማሪዎች በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ በሩሲያ ጋዜጠኞች ላይ በተፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የወንጀል ክስ ከፈቱ
19:25 05.01.2025 (የተሻሻለ: 19:44 05.01.2025)
ሰብስክራይብ