🪖 የሩሲያ ጦር ኬቭ በቤልጎሮድ ላደረሰችው የአቲሲምስ ጥቃት ምላሹ እንደማይቀር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
🪖 የሩሲያ ጦር ኬቭ በቤልጎሮድ ላደረሰችው የአቲሲምስ ጥቃት ምላሹ እንደማይቀር አስታወቀባለፈዉ አርብ የኬቭ አገዛዝ የአሜሪካውን አታሲምስ ሚሳኤል በመጠቀም በቤልጎሮድ  ክልል የሚሳኤል ጥቃት ለመፈፀም መሞከሩን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።" የሩሲያ የአየር መከላከያ ስረአቶች ባደረጉት ጠንካራ የአየር ዉጊያ ፤ ኤስ -400 ሳም (ከመሬት ወደ አየር ሚሳኤል) ሰረአት እና ፓንትሲራ ኤስኤም አባላት የአታሲምስ ሚሳኤልን መትተው ጥለዋል። ይህ በምእራባውያን የበላይ ጠባቂነት የተካሄደ የኬቭ ድርጊት ምላሽ ሳይሰጠው የሚቀር አይደለም" በማለት መግለጫው ይነበባል።ኬቭ በምእራባውያን በቀረበላት መሳሪያዎች ተጠቅማ በሩሲያ ግዛት ውስጥ ጥቃት እንድትፈፅም መፍቀድ የኔቶን ሀገሮች በግጭቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ ያደርጋቸዋል ፤ በማለት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቀደም ብሎ መናገራቸው ይታወሳል። በጎርጎሮሳዊያኑ ህዳር 17 ፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆን ባይደን ዩክሬን በአሜሪካ ሰራሹ አታሲምስ ሚሳኤል በመጠቀም ሩሲያን እንድታጠቃ ፍቃድ መስጠታቸውን ኒዩርክ ታይምስ ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ መንግስት ተወካይን ዋቢ በማድረግ ዘግቦ ነበር።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0