የአፍጋኒስታን የግል ትምህርት ቤቶች ህብረት ሴቶች በከፍተኛ ትምህርት ክፍሎች መማር እንዲፈቀድላቸው ጠየቀበአፍጋኒስታን አሁን ላይ ሴቶች በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ስድስተኛ ክፍል ድረስ ብቻ ነው እንዲማሩ የተፈቀደላቸው። " በየዕለቱ ትምህርት የማያገኙ ሴቶች ሁኔታ እየተባባሰ ሲሄድ እናያለን። እስላማዊ ባለሥልጣናትን ቁርዓን "በአላህ ስም አንብቡ" የሚለውን መመሪያ እንዲያከብሩ እንጠይቃለን። በአዲሱ 1404 የትምህርት ዓመት ትምህርት ቤቶች ለሴት ልጆቻችን እና እህቶቻችን እንዲከፈቱ እንፈልጋለን" ሲሉ የአፍጋኒስታን የግል ትምህርት ቤቶች ህብረት ኃላፊ አዚም ማይዳንዋል መናገራቸውን በሻምሻድ የዜና ፖርታል ዘግቧል።በአፍጋኒስታን ልጃገረዶች ትምህርት ቤት መሄድ አለመቻላቸው በስነልቦናቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል በማለት ማይዳንዋል ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በ3500 የግል የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ልጃገረዶች እየተማሩ እንደሚገኙ አክለው ገልጸዋል።የታሊባን ቃል አቀባይ የሆኑት ዛቢሁላህ ሙጃሂድ ለሜይዳንዋል ንግግር በሰጡት ምላሽ ትምህርት የመማር መብት ለሁሉም የአፍጋኒስታን ዜጎች አስፈላጊ እንደሆነና ለሴት ልጆች ትምህርት ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። "አንድ ሰው የአፍጋኒስታን ህብረተሰብን በቅርበት ቢመለከት በዚህ ጉዳይ ላይ አለመግባባት እንዳለ ግልጽ ይሆንለታል እናም እነዚህን የሃሳብ ልዩነቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት አወዛጋቢ ጉዳዮችን ማስወገድ ያስፈልጋል። በአንድ በኩል፣ (ለሴት ልጆች ትምህርት) አስፈላጊ እና ለመረዳት የሚቻል ነው። ለዚህ ችግር መፍትሄዎች እንዳሉ ቀደም ሲል ተናግሬያለሁ" ሲሉ ሙጃሂድ መግለጻቸው በዜና አውታሩ ተገልጿል። የታሊባን መንግስት በጎርጎሮሳውያኑ ነሐሴ 2021 ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 2022 መጨረሻ ድረስ የአፍጋኒስታን ሴቶች የመጓዝ፣ የመማር እና የመሥራት መብታቸውን በመገደብ የሴቶችን የሁለተኛ ደረጃ እና የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት አግዷል። ይህ እርምጃ ከብዙ አገራት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እነዚህን ገደቦች እንዲነሱ ጥሪ በማቅረብ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ገጥሞታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የአፍጋኒስታን የግል ትምህርት ቤቶች ህብረት ሴቶች በከፍተኛ ትምህርት ክፍሎች መማር እንዲፈቀድላቸው ጠየቀ
የአፍጋኒስታን የግል ትምህርት ቤቶች ህብረት ሴቶች በከፍተኛ ትምህርት ክፍሎች መማር እንዲፈቀድላቸው ጠየቀ
Sputnik አፍሪካ
የአፍጋኒስታን የግል ትምህርት ቤቶች ህብረት ሴቶች በከፍተኛ ትምህርት ክፍሎች መማር እንዲፈቀድላቸው ጠየቀበአፍጋኒስታን አሁን ላይ ሴቶች በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ስድስተኛ ክፍል ድረስ ብቻ ነው እንዲማሩ የተፈቀደላቸው። " በየዕለቱ ትምህርት... 05.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-05T16:20+0300
2025-01-05T16:20+0300
2025-01-05T16:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የአፍጋኒስታን የግል ትምህርት ቤቶች ህብረት ሴቶች በከፍተኛ ትምህርት ክፍሎች መማር እንዲፈቀድላቸው ጠየቀ
16:20 05.01.2025 (የተሻሻለ: 16:44 05.01.2025)
ሰብስክራይብ