የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካን በሚስጥር የሰጠችው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ዋቢ በማድረግ ፤ ዩክሬንን ጦር ለማስፈታት በቂ ምክንያት ነው አለ

ሰብስክራይብ
  የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካን በሚስጥር የሰጠችው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ዋቢ በማድረግ ፤ ዩክሬንን ጦር ለማስፈታት በቂ ምክንያት ነው አለ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን በትላንትናው እለት በታተመው የኒውዮርክ ታይምስ ቃለ መጠይቃቸው እንደተናገሩት ፤ ዋሽንግተን የሞስኮው ልዩ ኦፕሬሽን ከመጀመሩ በፊት በጎርጎሮሳዊያኑ 2021 በሚስጥር ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ አደርጋለች። " ሩሲያ ስለዚህ ጉዳይ ለአመታት ስትናገር ቆይታለች።  አሜሪካን እና ብሪታንያ ወደ ዩክሬን የጦር መሳሪያ እያስገቡ እንደሆነ ፤ ማለቂያ አልባ የነበረው በጥቁር ባህር አካባቢ  የሩሲያን ድንበር በመጣስ ሲደረጉ የነበሩ የኔቶ የጦር ልምምዶች እና በአደገኛ ሁኔታ በምእራባውያን የሲቪል አውሮፕላኖችን  እንደ የጦር አውሮፕላኖች በመጠቀም በሀገራችን የአየር ክልል ላይ የሚደረግ እንቅስቃሴ ...  ለዚህ ነው አንዱ የዚህ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን አላማ የዩክሬንን ጦር ትጥቅ ማስፈታት እና የሀገራችንን ደህንነት ማረጋገጥ የሆነው" በማለት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ማሪያ ዛክሃሮቫ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።ሞስኮ በተደጋጋሚ እንዳሳወቀችው ለዩክሬን የሚላኩ የጦር መሳሪያዎች እየተካሄደ ያለውን ግጭት ከማራዘም እንዲሁም የሚሞቱ የዩክሬን ወታደሮችን ቁጥር በእጅጉ ከማሳደግ ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም። ይበልጡን ፤ ማንኛውም ለዩክሬን የጦር መሳሪያ የተጫነበት ጭነት የሩሲያ ህጋዊ ኢላማ እንደሚሆን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0