የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአፋር ክልል ርዕደ መሬት ከተከሰተባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎችን በማስወጣት ላይ ናቸው

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአፋር ክልል ርዕደ መሬት ከተከሰተባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎችን በማስወጣት ላይ ናቸው"መንግስት ነዋሪዎችን ከርዕደ መሬት ማዕከል ለማስወጣት እየሰራ ነው" ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።መንግስት በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም በኢትዮጵያ ሰሜን ምስራቅ አፋር ክልል ውስጥ በሚገኙ 12 ቀበሌዎች ላይ  ከተለያዩ  የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አሰማርቷል፤  በእነዚህ ቀበሌዎች የሚኖሩ 80,000 ዜጎች እንዲወጡ እንደሚደረግ የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቱ አመልክቷል።"በአፋር፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተለያዩ መጠኖች ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል። ከጊዜ ወደ ጊዜ የክስተቶቹ መጠን እና ድግግሞሽ እየጨመረም ነው። በተለይ በዚህ ሳምንት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሬክተር ስኬል እስከ 5.8 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል ሲል" መግለጫው ገልጿል።ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ በትንሹ አስራ ሁለት ርዕደ መሬቶች በአፋር ክልል መመዝገቡን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬ (ዩኤስጂኤስ) አስታውቋል። አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ከአፋሯ አቦምሳ ከተማ 56 ኪሜ ርቀት ላይ 5.8 ማግኒቲዩድ ሆኖ የተመዘገበዉ ጠንካራው የርዕደ መሬት ሆኖ ተመዝግቧል። በጨመረው የመሬት እንቅስቃሴ ምክንያት በአካባቢው የሚገኙት የፈንታሌ እና ዶፋን እሳተ ጎሞራዎች እንዳይፈነዱ ስጋት ፈጥሯል። " በቅርቡ፤  በአፋር ክልል ፈንታሌ አካባቢ የታመቀ ውሀ እና እንፋሎት በዶፋን እሳተጎመራ አቅራቢያ ተፈጥሯል" በማለት የተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ የትስስር ገፁ ያስታወቀዉ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢኒስቲትዩት ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0