ሩሲያ እና አሜሪካ ከኒው ስታርት ስምምነት በኋላ የጦር መሳሪያ ክምችትን ለማስቀረት አዲስ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና አሜሪካ ከኒው ስታርት ስምምነት በኋላ የጦር መሳሪያ ክምችትን ለማስቀረት አዲስ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉየኒው ስታርት ስምምነት በጎርጎሮሳውያኑ 2026 የሚያበቃ መሆኑ በሩሲያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ስለወደፊቱ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ውይይት እንደገና እንዲቀጣጠል አድርጓል። ባለሙያዎች ለስፑትኒክ እንደገለጹት ሁለቱም አገሮች የኑክሌር የጦር መሳሪያ ውድድርን ተከትሎ የሚመጣውን አደጋና ወጪ ለመቀነስ አዲስ ስምምነት ለመፍጠር ጠንካራ ተነሳሽነት አላቸው። የድርድር ውስብስብነት ቢኖርም በስትራቴጂካዊ መረጋጋት እና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው የጋራ ፍላጎት ሁለቱንም ሀገሮች ወደ ስምምነት ሊያደርሳቸው ይችላል።በጎርጎሮሳውያኑ 2010 የተመሰረተው ኒው ስታርት ስምምነት፤ ስትራቴጂካዊ የኑክሌር ዎርሄዶችን እና የመላኪያ ስርዓቶችን ለመገደብ ወሳኝ ማዕቀፍ ሆኖ ያገለግላል። ሆኖም የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአሜሪካ ስምምነቱን አለማክበር እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት መሆኑን በመጥቀስ በጎርጎሮሳውያኑ የካቲት 2023 ጀምሮ  የሩሲያ ተሳትፎ ማገዳቸውን ተከትሎ ውጥረት ነግሷል። እንደ የኮርኔል ዩኒቨርሲቲው ሪቻርድ ቤንሰል ያሉ ባለሙያዎች፤ ምንም እንኳን በአገር ውስጥ አጀንዳዎች ተጽዕኖ በተለይም በትራምፕ አስተዳደር ስር ረዘም ያለ ድርድርን እንደሚደረግ ቢጠብቁም ስለ አዲሱ ስምምነት ተስፋ በተመለከተ አዎንታዊ ምልከታ አላቸው። በሁለቱም ወገኖች መካከል ስምምነት ላይ ለመድረስ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ወሳኝ ሊሆኑ ይችላሉ። ያሉትን የኑክሌር መሳሪያዎች መጠበቅና ማዘመን ከፍተኛ የገንዘብ ተግዳሮትን ይፈጥራል። የፖለቲካል ሳይንስ ባለሙያ የሆኑት ሮድሪክ ኪዊት ፣ የቀጣዩ ትውልድ የኑክሌር መሳሪያዎችን የማሰማራት ከፍተኛ ወጪ እንዳለው የገለጹ ሲሆን፣ ዋሽንግተን እና ሞስኮ አላስፈላጊ ወጪዎችን ማስወገድ እንደሚመርጡም ጠቁመዋል። እነዚህ የጋራ ጥቅሞች ቢኖሩም እንደ ቻይና ያሉ ሌሎች የኑክሌር ሀይሎች በተለያዩ ስትራቴጂካዊ ግቦች ምክንያት በወደፊቱ ስምምነቶች እንደሚካተቱ አይጠበቅም።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0