ሩሲያ በጋዛ ህፃናት ጉዳይ የተመድ ፀጥታው ምክርቤት ስብሰባ እንዲያደርግ ለመጠየቋን የተመድ መልእክተኛ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ በጋዛ ህፃናት ጉዳይ የተመድ ፀጥታው ምክርቤት ስብሰባ እንዲያደርግ ለመጠየቋን የተመድ መልእክተኛ ተናገሩ " በጋዛ ህፃናት ጉዳይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት የተናጠል ስብሰባ እንዲያደርግ ለመጠየቅ እቅድ አለን ፤ እንደ እድልሆኖ ምእራባውያን ባልደረቦቻችን ይህንን ለማጤን ፍቃደኛ አይደሉም ... " በማለት በተመድ የሩሲያ ቋሚ መልእክተኛ ቫሲልይ ኔቤንዘያ የፍልስጤምን ጥያቄ በተመለከ የተደረገ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።ኔቤንዘያ እየተካሄደ ባለው ግጭት እየማቀቁ ያሉ ፍልስጤማውያን ህፃናት ጉዳይ ቸል ያሉትን ምእራባውያንን " ራሳቸውን በሚጠቅም ጉዳይ ላይ ነው ትኩረታቸው" በማለት ወርፈዋቸዋል። ከጎርጎሮሳውያኑ ጥቅምት 2023 ጀምሮ በጋዛ ሰርጥ ከተገደሉት 43,500 ሰዎች መሀከል 70 በመቶዉ ህፃናት እና ሴቶች መሆናቸውን የተመድ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ በህዳር ወር ባወጣው ሪፖርት አሳውቆ ነበር።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0