ፕሬዝዳንት ሩቶ ፤ የኬንያ መንግስት ያለ ፍርድቤት ትዕዛዝ ግድያ መፈፀም እንዲቆም እና የህግ የበላይነት እንዲጠብቅ ሊያረጋግጥ ነው

ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ሩቶ ፤ የኬንያ መንግስት ያለ ፍርድቤት ትዕዛዝ ግድያ መፈፀም እንዲቆም እና የህግ የበላይነት እንዲጠብቅ ሊያረጋግጥ ነው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ— በዜጎች፣ በወንጀለኞች ወይም በፖሊስ የሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች- በጥልቀት እንደሚመረመሩ ቃል በመግባት፤  ያለ ፍርድቤት ትዕዛዝ የሚፈጸም ግድያ እንዲቆም አስተዳደራቸው ቁርጠኛ መሆኑን ዳግም አረጋገጡ። በቡንጎማ የብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሞሰስ ዌታንጉላ እናት የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ሩቶ፣ መንግስታቸው የህግ የበላይነትን እንደሚያከብር ለኬንያውያን አረጋግጠዋል። "ህግ በተመረጠ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን የለበትም ምክንያቱም የሕግ የበላይነት ዴሞክራሲያችንን የሚደግፍ ነው" ብለዋል።አበይት ቁርጠኝነት፤ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚፈጸሙ ግድያዎችን ማስቆም ፤ ሩቶ በያላ እና ታና ወንዞች ውስጥ የተገኙ አስከሬኖችን የመሳሰሉ ያለፉ ክስተቶች እንደማይደገም ቃል ገብተዋል።የፖሊስ ገለልተኝነት ፤ የብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት በጀቱን ከፕሬዝዳንቱ ቢሮ ወደ ኢንስፔክተር ጄኔራል በማስተላለፍ ገለልተኛ ሆኖ እንዲሠራ ለማድረግ የተደረጉ ጥረቶችን አጽንዖት ሰጥተዋል።የሕግ የበላይነት ፤ ፕሬዝዳንቱ ስርዓትን ማስጠበቅ ሁልጊዜ በህግ ማዕቀፎች የጠበቀ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። " ዴሞክራሲያችንን የምናስቀጥልበት መንገድ ይህ ነው" ብለዋል ሩቶ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0