በዙምባቤዌ ፖርክ ውስጥ የታየው የአዲስ አመት ተአምር ፤ የሰባት አመቱ ህፃን አምስት ቀናት ያህል አንበሶች ከሚበዙበት ፓርክ ቆይቶ በህይወት ተገኘ

ሰብስክራይብ
በዙምባቤዌ ፖርክ ውስጥ የታየው የአዲስ አመት ተአምር ፤ የሰባት አመቱ ህፃን አምስት ቀናት ያህል አንበሶች ከሚበዙበት ፓርክ ቆይቶ በህይወት ተገኘ ቲኖቴንዳ ፑንዳ ፤  ተብሎ የሚጠራው ይህ የሰባት አመት ወንድ ልጅ ለአምስት ቀን ከጠፋ በኋላ የአንበሳ መንጋዎች ፣ ነብሮች እና ዝሆኖች ባሉበት  በማቱሳንዳ ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ በህይወት መገኘቱን የዙምባቡዌ ፓርኮች እና የዱርህይወት አስተዳደር ባለስልጣን ዘግቧል። ከመኖሪያው በ 48 ኪሜ ርቀት ላይ የተገኘው ቲኖቴንዳ  በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ ፤ በከባድ ዝናብ እና የዱር አራዊት መሀከል በህይወት ሊወጣ የቻለው የዱር ፍራፍሬዎችን ለቅሞ በመብላት እና በዙምባብዌ ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች በሚታወቀው ውሀ ማግኛ መንገድ በወንዞች አካባቢ ውሀ ቆፍሮ እየጠጣ በመቆየቱ ነው። የልጁ ጉብዝና በዚህ አላበቃም ፤ በአካባቢው የሚገኙ አጥቂዎች በማይደርሱበት ሾላላ ድንጋይ ላይ ሲተኛ ቆይቷል።በመንደሩ ከበሮ መቺ መሪዎች ታግዞ የነበረው እረፍት አልባ ፍለጋ ሬንጀሮችን ፣ የአካባቢውን ነዋሪዎች እና ፖሊስን አጣምሮ በያዘ ሀይል ነበር ሲደረግ የቆየው ። ከነበረው አስቸጋሪ ሀኔታ በተቃራኒ ሬንጄሮች ቲኖቴንዳን ሲያገኙት ደክሞት የነበረ ሲሆን ያለ ምንም ጉዳት በተአምር ከፓርኩ መውጣት ችሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0