የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን በጥር ወር እንደሚጎበኙ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለፁ

ሰብስክራይብ
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን በጥር ወር እንደሚጎበኙ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለፁ "የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የፖለቲካ ቢሮ አባል እና የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከታህሳስ 27 እስከ ጥር 3 ናሚቢያን፣ ኮንጎ ሪፐብሊክን፣ ቻድን እና ናይጄሪያን በደረሳቸው ግብዣ መሠረት ይጎበኛሉ" ብለዋል ቃል አቀባይዋ ማኦ ኒንግ። የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ቤጂንግ፤ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ስትራቴጂካዊ የጋራ መተማመንን ለመፍጠር እና የንግድ ትብብሯን ለማጠናከር ዝግጁ ናት ሲሉ ከዚህ በፊት ተናግረዋል። ቻይና እኩል እና በስርዓት ላይ የተመሠረተ የባለብዙ ዋልታ ዓለምን፣ ሁሉንም የሚጠቅም አካታች ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትስስር መፍጠርን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ፍትህ እና ገለልተኛነትን በጋራ በመጠበቅ ዙርያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር አብራ ለመቆም ዝግጁ ናት ብለዋል። አፍሪካ በዘመናዊው ዓለም ጠቃሚ ዋልታ ናት ያሉት ሺ ጂንፒንግ፤ አህጉሪቱ ከቻይና ዲፕሎማሲ ቀዳሚ ትኩረቶች አንዷ መሆኗንም አፅንዖት ሰጥተው ጠቅሰዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0