ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሕብረት ግቦች እና ለፓን አፍሪካኒዝም እሳቤዎች ቁርጠኝነቷን አረጋገጠች ከየካቲት 8 እስከ 9 የሚካሄደውን 38ኛውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ከየካቲት 5 እስከ 6 የሚካሄደውን የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ፤ ለአፍሪካ ሕብረት እና ለፓን አፍሪካኒዝም እሳቤዎች ያላትን ቁርጠኝነት እያሳየች ነው ሲሉ፤ በአልጄሪያ የኢትዮጵያ መልዕክተኛ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ ለፒኦኤ ተናግረዋል። ሀገሪቱ ለአፍሪካ ሕብረት ግቦች ያላትን ቁርጠኝነት እና ይህን መሰል ትልቅ ስብሰባ በማዘጋጀቷ ኩራት እንደሚሰማት አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸው ተገልጿል። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና የአፍሪካ ሕብረት ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፤ ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎቿ ደረጃውን የጠበቀ መስተንግዶ ለማቅረብ ከፍተኛ የመሠረተ ልማት ማሻሻያዎችን አድርጋለች። አምባሳደር ሙክታር የከተማዋ የታደሰ ገጽታ የኢትዮጵያን የፓን አፍሪካኒዝም ምልክትነት የሚያንፀባርቅ መሆኑን አንስተዋል። ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ኢትዮጵያ በአህጉራዊ አንድነት እና እድገት የመሪነት ሚናዋን የበለጠ የምታጠናክርበት እድል መሆኑንም ጠቁመዋል። ዝግጅቱ ውጤታማ እንደሚሆን እምነታቸውን የገለጹት አምባሳደሩ፤ የኢትዮጵያን የነጻነት ታሪክ እና ለአፍሪካ የጋራ ለውጥ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያመለክት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሕብረት ግቦች እና ለፓን አፍሪካኒዝም እሳቤዎች ቁርጠኝነቷን አረጋገጠች
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሕብረት ግቦች እና ለፓን አፍሪካኒዝም እሳቤዎች ቁርጠኝነቷን አረጋገጠች
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሕብረት ግቦች እና ለፓን አፍሪካኒዝም እሳቤዎች ቁርጠኝነቷን አረጋገጠች ከየካቲት 8 እስከ 9 የሚካሄደውን 38ኛውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ከየካቲት 5 እስከ 6 የሚካሄደውን የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ... 03.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-03T18:27+0300
2025-01-03T18:27+0300
2025-01-03T18:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሕብረት ግቦች እና ለፓን አፍሪካኒዝም እሳቤዎች ቁርጠኝነቷን አረጋገጠች
18:27 03.01.2025 (የተሻሻለ: 18:44 03.01.2025)
ሰብስክራይብ