በ2024 በሁሉም የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ሀገራት የውጪ ቱሪስት ፍሰት ጨምሯል ሲሉ ዋና ፀሃፊው ተናገሩ

ሰብስክራይብ
በ2024 በሁሉም የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ሀገራት የውጪ ቱሪስት ፍሰት ጨምሯል ሲሉ ዋና ፀሃፊው ተናገሩ "በ2024 በአጠቃላይ የቱሪስት ፍሰት ብዛት፤ የውጭ ቱሪስቶች ማለት ነው፤ በሁሉም የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ሀገራት ውስጥ ጨምሯል ማለት ይቻላል። በአንዳንዶቹ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ20%፤ በአንዳንዶቹ እስከ 47% ጨምሯል። ይህ ትብብር በፍጥነት እያደገ መምጣቱን ያመላክታል" ሲሉ ዋና ፀሃፊው ኑርላን የርሜክባዬቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ለቱሪዝም ልማት አንድ የኤሌክትሮኒክስ መተግበሪያ መፍጠር፣ ድንበር ዘለል የቱሪስት መስመሮችን ማደራጀት እና መደበኛ መድረኮችን ማዘጋጀት የመሳሰሉ የድርጅቱ አባል ሀገራት ጅምሮች፤ ለቱሪዝም እድገት አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ ዋና ጸሃፊው ጠቁመዋል። የሻንጋይ ትብብር ድርጅት በ2001 የተመሰረተ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን ህንድ፣ ኢራን፣ ካዛኪስታን፣ ቻይና፣ ኪርጊስታን፣ ሩሲያ፣ ቤላሩስ፣ ታጂኪስታን፣ ፓኪስታን እና ኡዝቤኪስታንን ያጠቃልላል። አፍጋኒስታን እና ሞንጎሊያ ታዛቢ ሀገራት ናቸው። አዘርባጃን፣ አርሜኒያ፣ ባህሬን፣ ካምቦዲያ፣ ግብፅ፣ ኩዌት፣ ማልዲቭስ፣ ምያንማር፣ ኔፓል፣ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ቱርክ እና ስሪላንካ ደግሞ አጋር ሀገራት ናቸው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0