ኢትዮጵያ ለ2025 የብሪክስ ፕሬዝዳንት ብራዚል መልካም ምኞቷን ገለጸች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለ2025 የብሪክስ ፕሬዝዳንት ብራዚል መልካም ምኞቷን ገለጸች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ብራዚል በብሪክስ የፕሬዝዳንትነት ጊዜዋ ፍትሃዊ፣ አካታች እና ውጤታማ ዓለም አቀፍ አስተዳደር ለማራመድ፣ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር እና ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ለማሰባሰብ የሰነቀችውን ራዕይ እንደምትደግፍ አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ በ2025 የብሪክስ ፕሬዝደንትነትን ከተረከበችው ብራዚል ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላትም ሚኒስቴሩ ጠቅሷል፡፡ ሩሲያ በ2024 የብሪክስ ፕሬዝዳንትነት ጊዜዋ ለሰጠችው አርአያነት ያለው አመራር ኢትዮጵያ አድናቆት እንዳላትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጨምሮ ገልጿል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0