የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ሶማሊያን እንደጎበኙ፤ ይህም የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተረጋጋ መምጣቱን ያሳያል ተባለ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ሶማሊያን እንደጎበኙ፤ ይህም የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተረጋጋ መምጣቱን ያሳያል ተባለ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ሙሳ ሐሙስ ወደ ሶማሊያ ያደርጉት ጉዞ፤ ኢትዮጵያ በራስ ገዟ ሶማሌላንድ የባሕር ኃይል ሰፈር ለመመሥረት ማቀዷን ተከትሎ ከተፈጠረው ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በኋላ፤ የመጀመሪያው ከፍተኛ ደረጃ የሁለትዮሽ ጉብኝት ነው። የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር፤ ጉብኝቱን ለምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን ቢያረጋግጡም፤ የውይይቱ ዝርዝር መረጃ ግን አልተገለጸም። ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ከነበረበት ወቅት በኋላ የመጣ ነው። ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችውን ስምምነት የማትቀለብስ ከሆነ አል-ሻባብን* በሚዋጋው የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ልዑክ አካል የሆኑት የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሀገሪቱ እንዲወጡ የሶማሊያ መንግሥት ጠይቋል። በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል የተደረገው ስምምነት፤ ኢትዮጵያ የሶማሊላንድን የባህር ጠረፍ ለባህር ኃይል ጦር ሰፈር እና የንግድ ወደብ በሊዝ መከራየት እንደምትችል ያስቀምጣል። ሞቃዲሾ ይህ ጠብ አጫሪነት እና ለሶማሊላንድ ነፃነት እውቅና የሚሰጥ ነው ስትል ስጋቷን ስትገልጽ ቆይታለች። ለወራት ከዘለቀ ውጥረት እና ያልተሳኩ ዓለማ አቀፍ የሽምግልና ሙከራዎች በኋላ፤ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ታህሳስ 2 ቀን በቱርክ በተደረገ ውይይት ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፤ የካቲት ወር ይጀምራል በተባለው ቴክኒካዊ ድርድር ልዩነታቸውን ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል። * በሩሲያ እና ሌሎች በርካታ ሀገራት የታገደ አሸባሪ ድርጅት ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0