13 የኮንጎ ወታደሮች በሰሜን ኪቩ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ተላለፈባቸው የሰሜን ኪቩ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የ23 ወታደሮችን ጉዳይ ባሳለፍነው ሳምንት መርምሯል። 13 ወታደሮች ከኤም23 ሚሊሻ ፊት በመሸሽ፣ በግድያ እና በዝርፊያ የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው ሲሆን፤ ሌሎች አራት ወታደሮች ደግሞ ስርቆትን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች ከሁለት እስከ አስር ዓመት እስር ተላልፎባቸዋል። ወታደሮቹ በሩዋንዳ መከላከያ ኃይል ይደገፋሉ ከሚባሉት የኤም23 አማፂያን ጋር ጦርነት እየተካሄደ ባለበት ወቅት ሸሽተዋል ተብሏል። "ከእነዚህ ወንጀለኞች መካከል 13ቱ በግድያ፣ በከበባ ግዜ ዝርፊያ በማካሄድ እና ፈሪነትን ጨምሮ ጥፋተኛ በመባላቸው የሞት ፍርድ ተላልፎባቸዋል። ሌሎች አራት ወታደሮች የጦር መሳሪያን በማጥፋት፣ ትእዛዝ በመጣስ እና በቀላል ስርቆት ወንጀል ተፈርዶባቸዋል" ሲሉ በክልሉ የኮንጎ ጦር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ማክ ሃዙካይ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። በኮንጎ ኃይል እና በኤም23 አማፂያን መካከል እየተካሄደ በሚገኘው ከፍተኛ ጦርነት ምክንያት በቅርብ ወራት ውስጥ በርካታ የወታደራዊ ፍርድ ሂደቶች ተከፍተዋል። የኤም23 አመፅ እንደገና ማገርሸቱን ተከትሎ ወታደሮች በመሸሽ እና ሌሎች ጥሰቶች ተከሰዋል። የአሁኑ የቅጣት ውሳኔ በታህሳስ ወር 2024 በሉቤሮ ውስጥ የተደረገውን ጦርነት የተመለከተ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
13 የኮንጎ ወታደሮች በሰሜን ኪቩ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ተላለፈባቸው
13 የኮንጎ ወታደሮች በሰሜን ኪቩ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ተላለፈባቸው
Sputnik አፍሪካ
13 የኮንጎ ወታደሮች በሰሜን ኪቩ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ተላለፈባቸው የሰሜን ኪቩ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የ23 ወታደሮችን ጉዳይ ባሳለፍነው ሳምንት መርምሯል። 13 ወታደሮች ከኤም23 ሚሊሻ ፊት በመሸሽ፣ በግድያ እና በዝርፊያ የሞት ቅጣት... 02.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-02T16:59+0300
2025-01-02T16:59+0300
2025-01-02T17:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
13 የኮንጎ ወታደሮች በሰሜን ኪቩ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ተላለፈባቸው
16:59 02.01.2025 (የተሻሻለ: 17:14 02.01.2025)
ሰብስክራይብ