አልጄሪያ የጥር ወር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነቷን ጀመረች

ሰብስክራይብ
አልጄሪያ የጥር ወር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነቷን ጀመረች አልጄሪያ ይህን አጋጣሚ ተጠቅማ የመካከለኛው ምስራቅ ግጭቶችን እና የአፍሪካን የፀጥታ ሁኔታ የሚመለከቱ ጉዳዮችን ለማራመድ እንደምትጠቀምበት ገልጻለች። በመጀመርያ ቅድሚያ የምንሰጠው በፍልስጤም ጉዳይ ለውጥ ማምጣት ነው ሲሉ፤ የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ቀደም ብለው ተናግረዋል። ሚኒስትሩ አክለውም አልጄሪያ የፀጥታውን ምክር ቤት ከተቀላቀለችበት ቀን ጀምሮ፤ ለፍልስጤም ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጥ እርምጃዎች በመውሰድ እንደምትታወቅ አመልክተዋል። በአፍሪካ ሽብርተኝነትን መዋጋት እና በአረብ ሊግ እና በተባበሩት መንግሥታት መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ሌሎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው። እነዚህን ግቦች ለማሳካት አልጄሪያ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሚገኙበት ክፍት የሚኒስትሮች ውይይት ለማዘጋጀት አቅዳለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0