አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና መረጋጋት ተልዕኮ በይፋ ስራ ጀመረ "በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2767 (2024) መሠረት ከጥር 1 ቀን 2025 ጀምሮ ኤዩሶም ወደ ስራ ገብቷል" ሲሉ በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ልዩ ተወካይ ሞሐመድ ኤል-አሚን ሶፍ አስታውቀዋል። "የሶማሊያን ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ በአትሚስ (የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ) የተገኙ ድሎችን ያስቀጥላል" ብለዋል። እንደ ሶፍ ገለፃ የአፍሪካ ሕብረት በሰላምና ፀጥታው ምክር ቤት በኩል፤ ለኤዩሶም እና ሶማሊያ ጦር የሚያደርገውን ድጋፍ ይቀጥላል። ባለፈው ዓመት ከአትሚስ የተዛወሩት የጦር ሰፈሮች፤ የሰላም አስካባሪ ኃይሉ ሶማሊያ ውስጥ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን አቅሙ እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት፤ የአሸባሪ ቡድኖችን ጥቃት ለመመከት ድጋፍ እሻለው በማለት የሶማሊያ መንግሥት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት፤ አትሚስ በኤዩሶም እንዲተካ ወስኗል። የሀገሪቱ ጦር ወደ 32,000 የሚጠጉ ወታደሮች ሲኖሩት፤ የሶማሊያ መንግሥት 11,000 የሚሆኑ የሰለጠኑ ወታደሮች እጥረት እንዳለበት ለአፍሪካ ሕብረት አስታውቋል። ለዚህም ከፍተኛ ውጊያ እና የወታደሮች መመናመንን በምክንያትነት አቅርቧል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና መረጋጋት ተልዕኮ በይፋ ስራ ጀመረ
አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና መረጋጋት ተልዕኮ በይፋ ስራ ጀመረ
Sputnik አፍሪካ
አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና መረጋጋት ተልዕኮ በይፋ ስራ ጀመረ "በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2767 (2024) መሠረት ከጥር 1 ቀን 2025 ጀምሮ ኤዩሶም ወደ ስራ ገብቷል" ሲሉ በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ልዩ... 01.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-01T19:07+0300
2025-01-01T19:07+0300
2025-01-01T19:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий