በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሕገ-ወጥ ንግድን በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን የሀገሪቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አስታወቀ በኢትዮጵያ መንግሥት ከሐምሌ ወር ጀምሮ መተግበር የጀመረው ሁሉን አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፤ ሕገ-ወጥ ንግድን በከፍተኛ ደረጀ እንደቀነሰ፤ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው ሶስተኛው ብሔራዊ የፀረ-ሕገ-ወጥ ንግድ ጉባዔ ላይ ተናግረዋል። ሕገ-ወጥ ንግድ በኢኮኖሚው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት አጽንኦት በመስጠት የተናገሩት ሚኒስትሩ፤ ገቢ ስወራ፣ ምርት ደብቆ ማቆየት እና ሌሎች ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች በኢትዮጵያ የንግድ ስርዓት ላይ ችግር እየፈጠሩ እንደሆነ ጠቁመዋል። የኮንትሮባንድ ንግድ የህዝብን ሀብት እያባከነ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ሆኖም መንግሥት እየተከተለ ባለው ፖሊሲ ሕ-ወጥ ንግድ እንደቀነሰ እና ከ108,000 በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል። መንግሥት ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ ባካሄደው ማሻሻያ፤ የምግብ የዋጋ ግሽበት ከ29.2% ወደ 20% ዝቅ ያለ ሲሆን፤ የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ከ18 ሚሊየን ዶላር ወደ 20 ሚሊዮን ዶላር አድጓል። በ2016 15.5 ቢሊየን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ መያዙንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሕገ-ወጥ ንግድን በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን የሀገሪቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አስታወቀ
በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሕገ-ወጥ ንግድን በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን የሀገሪቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አስታወቀ
Sputnik አፍሪካ
በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሕገ-ወጥ ንግድን በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን የሀገሪቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አስታወቀ በኢትዮጵያ መንግሥት ከሐምሌ ወር ጀምሮ መተግበር የጀመረው ሁሉን አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፤... 01.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-01T18:21+0300
2025-01-01T18:21+0300
2025-01-01T18:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሕገ-ወጥ ንግድን በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን የሀገሪቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አስታወቀ
18:21 01.01.2025 (የተሻሻለ: 18:44 01.01.2025)
ሰብስክራይብ