አንድ የአፍሪካ ሀገርን ጨምሮ ከጥር 1 ጀምሮ ዘጠኝ ሀገራት ብሪክስን በአጋርነት ተቀላቀሉ

ሰብስክራይብ
አንድ የአፍሪካ ሀገርን ጨምሮ ከጥር 1 ጀምሮ ዘጠኝ ሀገራት ብሪክስን በአጋርነት ተቀላቀሉ የደቡባዊ ዓለም ሀገራትን ጨምሮ ከታች የተዘረዘሩት ሀገራት ከሞላ ጎደል ሁሉንም አህጉራት ይወክላሉ፦ ቤላሩስ ቦሊቪያ ኢንዶኔዥያ ካዛኪስታን ኩባ ማሌዢያ ታይላንድ ኡጋንዳ ኡዝቤኪስታን ባለፈው ጥቅምት ወር በካዛን በተካሄደው የድርጅቱ ጉባኤ ላይ "የአጋር ሀገራት" ምድብ ይፋ ሆኗል። የሀገራቱን በአጋርነት መቀላቀል አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ አዲስ ከተቀላቀሉት ሀገራት ጋር የቅርብ ትብብር ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑን፤ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ሩሲያ በብሪክስ የፕሬዝዳንትነት ሊቀመንበርነቷ ለአዲሰ አባልነት መስፈርት ለማዘጋጀት ቅድሚያ በመስጠት፤ ይህን የትብብር ፎርማት ስብስቡን ለማስፋት የተሻለ አማራጭ አድርጋ እንደወሰደች፤ የሩሲያ ፕሬዝዳንት አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ ተናግረዋል። በካዛን ከሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ቀደም ብሎ 35 ሀገራት የብሪክስ አባል ለመሆን ማመልከቻ አስገብተው እንደነበርም ጠቁመዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0