የኮትዲቯር ፕሬዝዳንት የፈረንሳይ ጦር በጥር ወር ሀገሪቱን ለቆ እንደሚወጣ አስታወቁ

ሰብስክራይብ
የኮትዲቯር ፕሬዝዳንት የፈረንሳይ ጦር በጥር ወር ሀገሪቱን ለቆ እንደሚወጣ አስታወቁ በአቢጃን አካባቢ በፖርት-ቡት የሚገኘው የፈረንሳይ ጦር ሰፈር፤ 43ኛው የባህር ኃይል እግረኛ ሻለቃ በጥር ወር ለኮትዲቯር መከላከያ ኃይል እንደሚዘዋወር፤ ፕሬዝዳንት አላሳን ኦታራ አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል። "ዘመናዊነቱ አሁን ውጤታማ እየሆነ በመጣው ሰራዊታችን ኩራት ይሰማናል። በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ የፈረንሳይ ጦር በታቀደ እና በተቀናጀ መልኩ ከኮትዲቯር እንዲወጣ ወስነናል" ብለዋል። የጦር ሰፈሩ በኮትዲቯር ጦር የመጀመሪያ ዋና አዝዥ በጄኔራል ኦታራ ቶማስ ደአኪን ስም እንደሚጠራም ገልጸዋል። ወደ 1,000 የሚጠጉ ወታደሮች በ43ኛው የባህር ኃይል እግረኛ ሻለቃ ከወዲሁ መሰማራታቸውንም አስታውቀዋል። ፈረንሳይ ከሶስት የሳህል ሀገራት ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ እና ኒጀር ቀድማ ለቃ ወጥታላች። በታህሳስ 2024 ሴኔጋል እና ቻድ የፈረንሳይ ወታደሮች ከግዛታቸው እንደሚለቁ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0