የሩሲያ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ከአውሮፓ ህብረት አቻዎቻቸው የበለጠ ለመረጃ ቅርብ ናቸው ሲል የማህበራዊ ትስስር ገጹ መሰራች ተናገረ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ከአውሮፓ ህብረት አቻዎቻቸው የበለጠ ለመረጃ ቅርብ ናቸው ሲል የማህበራዊ ትስስር ገጹ መሰራች ተናገረ የቴሌግራም መስራች ፓቬል ዱሮቭ የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን የቴሌግራም ቻናሎች፤ የአርቲ እና ስፑትኒክን የሚያጠቃልለው የሮሲያ ሴጎድኒያ ሚዲያ ቡድን አባል አርአይኤ ኖቮስቲን ጨምሮ፤ በቅርቡ በዲጂታል አገልግሎቶች ሕግ እና ማእቀቦች አማካኝነት መታገዳቸውን ጠቅሷል። "ሆኖም ሁሉም የምዕራባውያን የሚዲያ ቴሌግራም ቻናሎች ሩሲያ ውስጥ በነፃነት ተደራሽ ናቸው […] በ2025 የሩሲያ ቴሌግራም ተጠቃሚዎች ከአውሮፓውያን የበለጠ ነፃነት ይኖራቸዋል ብሎ ማን ይገምታል?" ሲል በለጠፈው የቴሌግራም ጽሑፍ፤ በሁለቱ ክልሎች መኻከል ባለው የመረጃ ተደራሽነት እና ነፃነት ዙርያ ከሚሰማው ወሬ ጋር ፍጹም ተቃራኒ የሆነ ሃሳብ አቅርቧል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0